NEWS

የ 2009 ዓም 11ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓል በካናዳ በሚገኙት በኦታዋ እና በቶሮንቶ ከተሞች ተከበረ

By Admin

December 22, 2016

የ 2009 ዓም 11ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓል በካናዳ በሚገኙት በኦታዋ እና በቶሮንቶ ከተሞች ተከበረ

ክብርት አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ባደረጉት ንግግር የዘንድሮውን በዓል ልዩ የሚያደርገው ባሳለፍነው ዓመት በአገራችን ተከስቶ የነበረው ሁከት በህዝባችን ተሳትፎ ተወግዶ መንግስትም ጥልቅ የተሀድሶ እርምጃ መውሰድ በጀመረበት ወቅት የሚከበር መሆኑ እንደሆነ ጠቅሰው ይህ የተሀድሶ እርምጃ የተሳካ እንዲሆን እና የአገራችን ህዳሴ እንዲቀጥል ዳያስፖራችን በውስጡ ያሉ ጥቂት ድንፈኞችን በጽናት መታገል ጨምሮ አገራችን እያካሄደች ላለው የልማት፣ የዴሞክራሲና የሰላም ጥረቶች የበኩሉን አስተዋጽኦ ማድረጉን እንዲቀጥል ጥሪ አድርገዋል። ከዚህ ጋር በማያያዝም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ሕገ-መንግስት የአገራችን ብሔር ብሔረሰቦች ለዘመናት ተነፍገው የነበሩትን ሁለንተናዊ እኩልነታቸውን ያጐናፀፋቸው በመሆኑ እንደ ዐይን ብሌናቸው እንደሚጠብቁት ገልፀው በካናዳ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያንም በአገር ቤት ያለው ሕዝባችን አካል እንደመሆናቸው መጠን ጨቋኝ ስርዓቶችን ለመጣል በተደረገው እልህ አስጨራሽ ትግል የበኩላቸውን ሚና እንደተጫወቱ ሁሉ በትግሉ የተጐናፀፍነውን ሕገ-መንግስት መጠበቅ እንዳለባቸው ጠቅሰው ለቀጣዩ ትግል ጥሪአቸውን አቅርበዋል።

PressReleaseN