Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ጀግናው አትሌት ምሩፅ ይፍጠር ከዚህ አለም በሞት ተለየ ።

0 2,236

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ጀግናው አትሌት ምሩፅ ይፍጠር ከዚህ አለም በሞት ተለየ ። በካናዳ ሰአት አቆጣጠር ከምሽቱ 9 ሰአት ላይ ማረፉን የኢትዮጵያ ኢምባሲ በካናዳ አረጋግጦል ። ማርሽ ቀያሪው ምሩፅ ይፍጠር አገሩን ያስጠራ ብርቅ ኢትዮጵያዊ በካናዳ ቶሮነቶ በህክምና ሲረዳ ቆይቶ በዛሬው እለት ማረፉን አረጋግጠናል ። በ1972 ዓ.ም በሞስኮ በተካሄደው ኦሎምፒክ በ10,000 እና 5000 ተወዳድሮ ሁለት ወርቅ በማስመዝገብ ማርሽ ቀያሪው በመባል ይታወቃል። 1964 ዓም በተካሄደው ኦሎምፒክ በ10,000 ሜትር የነሐስ ሜዳሊያ አስመዝግቧል፡፡ አትሌቱ 1965 በተካሄደው የመላ አፍሪካ ጨዋታ አንድ ወርቅ በ10,000 እና አንድ ነሐስ በ5000 ሜትር ለሀገራችን አስመዝግቧል፡፡ በ1969 ዓ.ም በተካሄደው የመላ አፍሪካ ጨዋታ በ5000እና በ10,000 ሁለት ወርቅ በማስመዝገብ ድንቅ ብቃቱን ያሳየ እና የሀገራችን ስም በአለም ያስጠራ አትሌት ነው። አትሌት ምሩፅ ይፍጠር ባጋጠመው የጤና ችግር በህክምና ሲረዳ ቆይቶ በዛሬው እለት ህይወቱ አልፏል። ዝግጅት ክፍላችን ለቤተሰቦቹ እና ለመላው ኢትዮጵያውያን መፅናናትን ይመኛል

The Embassy of the Federal Democratic Republic of Ethiopia to Canada expresses its deepest condolences by the death of the Legendary Athlet Miruts Yifter. Miruts Yifter was very well known by a long distance track race. He was world champion who made his country proud and made Ethiopia’s flag high. Our heart felt sympathy goes out to his family and all Ethiopians and to all his fans.

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy