Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ከሀረር ከተማ ነዋሪዎች ጋር ተወያዩ

0 484

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ከሀረር ከተማ ነዋሪዎች ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ከሀረር ከተማ ነዋሪዎች ጋር ተወያዩ

ለ11ኛው የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በዓል በሀረር የተገኙት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ ከከተማዋ ነዋሪዎች ጋር ተወያዩ።

በውይይቱ ላይ የከተማዋን ነዋሪዎች የወከሉ የሀገር ሽማግሌዎችም የፌደራሉ መንግስት ለክልላቸው ልማት እስካሁን ላደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ይህ የፌደራል መንግስት ድጋፍ እንዲቀጥል የጠየቁት የሀገር ሽማግሌዎቹ፥ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የተለያዩ ጥያቄዎችን አንስተዋል።

ከተነሱት ጥያቄዎች መካከልም በአሁኑ ወቅት የሀረር ከተማ የቱሪስት እና የህክምና ማዕከል እየሆነች በመምጣቷ የራሷ የአውሮፕላን ማረፊያ ቢገነባላት የሚለው ይግኝበታል።

እንዲሁም “ የተቀላጠፈ እና አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ሀይል እንድናገኝ ክልሉ ሪጅናል ዲስትሪክት ቢኖረው፣ በርካታ የስራ አድል ፈጥሮ የነበረው እና አሁን የተቋረጠው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ዳግም ቢጀመር፣ በወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ ላይ እና የከተማዋን የውሃ አቅርቦት አስተማማኝ ለማድረግ ለክልሉ ድጋፍ ቢደረግ” የሚሉት ይግኛሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይልማርያም በምላሻቸው የተነሱት ጥያቄዎች መነሻቸው ምክንያታዊ እና ተገቢ መሆናቸው ገልፀዋል።

የተጀመሩት የልማት ስራዎች እንዲቀጥሉ የፌደራል መንግስት የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ነው ያረጋገጡት።

በሀረር ከተማ መንግስት የአውሮፕላን ማረፊያ መገንባት በእቅዱ ውስጥ እንደሌለ የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ሆኖም አሁን ያለውን የከተማዋን ሁኔታ ከግምት በማስገባት ግን የመገንባት እቅድን ያጤናል ብለዋል።

ከተማዋን የህክምና መስጫ ማዕከል የማድረግ አቅም ያለው እና 1 ሺህ አልጋዎች የሚኖሩት ሆስፒታል ግንባታ እንዲፋጠን መንግስት ድጋፍ እንደሚያደርግም አረጋግጠዋል።

በሀረር የኤሌክትሪክ ሀይል ሰብ ስቴሽን የመክፈት እቅዱ በሁለተኛው የአድገት እና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ውስጥ መካተቱን በማንሳት ይህም ፈጥኖ ወደ ተግባር እንዲገባ ይደረጋል ብለዋል።

የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታን በተመለከተ ፕሮጀክቱ ቆሞ የነበረው በክልሎች ሌሎች ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ስለነበሩ መሆኑን የተናገሩት አቶ ሀይልማርያም፥ አሁን ግን ይህ ፕሮጀክት በስፋት እንደሚቀጥል አመልክተዋል።

መንግስት ለወጣቶች ሰፊ የስራ እድል ለመፍጠር የነደፈው ፕሮጀክትም የሀረሪ ክልል ወጣቶችንም ተጠቃሚ እንደሚያደርግ አንስተዋል።

የሀረሪ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሙራድ አብዱላሂ በበኩላቸው የሀረርን ከተማ ወደ ቀደመ ገናናነቷ ለመመለስ አሁን በዓሉን መሰረት አድርጎ የተሟሟቀውን የልማት ስራ ለማስቀጠል የክልሉ መንግስት ይሰራል ብለዋል።

ጥያቄ ያነሱት የሀገር ሽማግሌዎች “የፌደራልም ሆነ የክልሉ መንግስት ልማትን ለማስቀጠል የሚያደርጉትን ጥረት ለመደገፍ ዝግጁ ነን” ብለዋል።

 

በባሃሩ ይድነቃቸው

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy