Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ኢትዮጵያ በህገ ወጥ ስደትና የስደተኞች ጉዳይ ላይ በትብብርና ምክክር ለሚሰራ ኮሚቴ ሊቀመንበር ሆነች

0 449

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ኢትዮጵያ በህገ ወጥ ስደትና የስደተኞች ጉዳይ ላይ በትብብርና ምክክር ለሚሰራ ኮሚቴ ሊቀመንበር ሆነች

ኢትዮጵያ በህገ ወጥ ስደትና የስደተኞች ጉዳይ ላይ በትብብርና ምክክር ለሚሰራ ኮሚቴ ሊቀመንበር ሆነች

አዲስ አበባ ታህሳስ 7/2009 ኢትዮጵያ  በአፍሪካ ቀንድ ህገ ወጥ ስደትና የስደተኞች ጉዳይ ላይ አተኩሮ በትብብርና ምክክር ዙሪያ የሚሰራ”ካርቱም ፕሮሰስ” የተሰኘ ኢንሼቲቭ ኮሚቴ የሊቀ መንበርነቱን ቦታ ተረከበች።

ኢንሼቲቩ በአፍሪካ ቀንድ ህገ ወጥ የስደት እቅስቃሴን ለመግታትና ለስደተኞች ጊዜያዊና ዘላቂ መፍተሄ ለማበጀት በአውሮፓ ህብረትና በአፍሪካ ቀንድ ተነሳሽነት የተመሰረተ ኮሚቴ የሚመራ ነው።

የኮሚቴ የከፍተኛ ባለስልጣናት የጋራ ስብሰባ ዛሬ በአዲስ አበባ ተካሂዷል።

“ካርቱም ፕሮሰስ” እ.አ.አ በ2014 የአፍሪካ ቀንድና የአውሮጳ ህብረት በጋራ ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርና ስደት ላይ በመወያየት ተጨባጭ ፕሮጀክቶችን በመንደፍ ስደተኞች ባሉበት አገር የተረጋጋ ህይወት እንዲመሩ ለማስቻል ታስቦ የተቋቋመ ነው።

ኮሚቴው በየዓመቱ  ሊቀ መንበሩን የሚቀይር ሲሆን፤ ኢትዮጵያ ለአንድ ዓመት የምትቆይበትን ሊቀ መንበርነት ዛሬ ከእንግሊዝ ተረክባለች።

ኢትዮጵያ ስደትን ለመግታት፣ አገርን በማልማት  ድህነት ለመቀነስና የስራ አጥነትን ችግር ለማቃለል በመስራት ላይ መሆኗ፤ እንዲሁም ባላት አቅም የሌሎች አገሮች ስደተኞችን ተቀብላ ማስተናገዷ ቦታው እንዲሰጣት ካደረጉ ጉዳዮች መካከል ተጠቃሾች ናቸው።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ በስብሰባው እንደተናገሩት “አገሬ በሊቀ መንበርነት በምትመራበት ጊዜ ካርቱም ፕሮሰስ የጋራ ፕሮጀክት ይበልጥ እንደሚጠናከር አልጠራጠርም” ብለዋል።

ኢትዮጵያ የስደተኞች ምንጭ፣ መዳረሻና መተላለፊያ መሆኗን የጠቆሙት ዶክተር ወርቅነህ፤  በአፍሪካ ቀንድና አውሮጳ ህብረት መካከል በሚኖረው ትብብር ውስጥ ወሳኝ ሚና እንደሚኖራት ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ 800 ሺ የሚጠጉ ስደተኞችን እያስተናገደች መሆኗን የገለጹት ሚኒስትሩ፤ አደገኛ የስደት ጉዞ የሚያደርጉና በሕገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ወንጀል የሚፈጸምባቸው ኢትዮጵያውያን መኖራቸውንም ጠቁመዋል።

በኢትዮጵያ ህገወጥ ስደት አገራዊ ጉዳይ መሆኑ ጠቅሰው፤ መንግስትም መሰረታዊ የስደት መንስኤዎችን በመለየት ለመፍታትና የስራ አጥነትን ችግር ለማቃለል እየሰራ መሆኑን አስረድተዋል።

በተጨማሪም ህገ ወጥ ስደትን ለመከላከል አዲስ ህግ መውጣቱን አውስተው፤  እስካሁን በተደረገው ቁጥጥር አንድ ሺ  የሚሆኑ ህገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ለፍትህ መቅረባቸውን አስረድተዋል።

ከተለያዩ አገሮች ወደ ኢትዮጵያ ለሚገቡ ስደተኞች ወደቀጣይ አገር የሚያደርጉትን ስደት ለመቀነስ የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ነው የገለጹት።

በዚሁ መሰረት በአገሪቷ ከተሞች የትምህርት ተጠቃሚና የሙያ ባለቤት እንዲሆኑ ለማድረግ የሚያስችል አዲስ ፖሊሲ መጀመሯንም ተናግረዋል።

የሊቀ መንበርነት ቦታውም አገሪቷ የራሷና የጎረቤት አገሮች የስደት ችግር እንዲፈታ የተሻለ ስራ የመስራት ጥሩ አጋጣሚ ነው ብለዋል።

“በአዲሱ ፖሊሲ ለስደተኞች 30 በመቶ የሚሆን የስራ እድል ይሰጣል” ያሉት ዶክተር ወርቅነህ፤ ለስደተኞች የስራ እድል ፈጠራ ጉዳይ ለአንድ አገር ብቻ የሚተው ሳይሆን የአለም ዓቀፍ ትብብር የሚሻ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

በአውሮጳ ህብረት የስደተኞች ጉዳይ ዳይሬክተር ብላንካ ሮድሪጉዝ በበኩላቸው እንደገለጹት፤ ኮሚቴው ስደተኞች ወደተለያዩ አገሮች የስደት ጉዞ በሚያደርጉበት ወቅት ለህይወታቸው ዋስትና ስለማይኖራቸው ለተለያዩ ችግሮች እንዳይጋለጡ ጠንክሮ መስራት ይጠበቅበታል።

ህብረቱም ስደተኞች በደረሱበት አገር ተረጋግተው ህይወታቸውን ለመምራት እንዲችሉና ወደ ሁለተኛ የስደት አገር በሚያደርጉት ጉዞ የሚገጥማቸውን ችግር ለመከላከል  እንደሚሰራ ተናግረዋል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy