ሲጋራ በማጨስ በየአመቱ አለም 1 ትሪሊዮን ዶላር እንደምታጣ የአለም ጤና ድርጅት አስታወቀ
ሲጋራ በማጨስ በየአመቱ አለም 1 ትሪሊዮን ዶላር እንደምታጣ የአለም ጤና ድርጅት አስታወቀ፡፡
የአለም ጤና ድርጅት ባካሄደው ጥናት የሲጋራ አጫሾች ቁጥር በማሻቀብ ላይ መሆኑን ጠቅሶ ፣ይህም የአለም ስጋት
እየሆነ መምጣቱን አመልከቷል፡፡
አዲሱ ጥናት እንዳመለከተው በሚቀጥሉት አመታት ከማጨስ ጋር በተያያዘ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር መጨመሩንም አሳይቷል፡፡
በአሁን ሰአት በአለም ላይ ከሲጋራ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ ስድስት ሚሊዮን ሰዎች በየአመቱ እንደሚሞቱ ያሰቀመጠው ጥናቱ፣ ይህ ቁጥር ግን እኤአ በ2030 እስከ 8 ሚሊዮን ከፍ ሊል እንደሚችል የአለም ጤና ድርጅት ስጋቱን ገልጿል፡፡
ከማጨስ ጋር በተያያዘ በምርታማነት ደረጃና በጤና አገልግሎት ላይ ከሚከሰቱ አሉታዊ ምክንያቶች የተነሳ በየአመቱ ቢያንስ እስከ 1 ትሪሊየን ዶላር በአለም ኢኮኖሚ ላይ ኪሳራ እንደሚያስከትል ጥናቱ አረጋግጧል፡፡
በመካከለኛ እና ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ባላቸው ሀገሮች ከማጨስ ጋር በተያያዘ 80 በመቶ በላይ ሰዎች እንደሚሞቱ የተገለፀ ሲሆን፣ የአጫሾች ቁጥር በጨመረ መጠን የሟቾች ቁጥር እንደሚጨምርም ጥናቱ አክሏል፡፡
የአለም ጤና ድርጅት እንደገለፀው አብዛኛዎቹ ሀገራት ጤናማ ኑሮ ለማስፈንና የሲጋራ አጠቃቀምን ለመቀነስ በስጋራ ገበያዎች ላይ ክልከላ፣ በሲጋራ እሽጎች ላይ ማስጠንቀቂያ እና የዋጋ ጭማሪ ቢያደርጉም ለወጡ ግን እምብዛም ነው፡፡
በ2013/14 በአለም ላይ ከሲጋራ ቀረጥ የተገኘው ገቢ 269 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን በሲጋራ ምክንያት ከተፈጠረውን የአለም ኢኮኖሚ ክስረት ጋር ሲስተያይ ኪሳው የገዘፈ በመሆኑ ችግሩ የሚያደርሰውን ጉዳት ለመከላከል መንግስታት ተጨባጭ እርምጃ እንዲወስዱ ድርጅቱ አሳስቧል፡፡
የጤና ባለሙያዎች የትምባሆ አጠቃቀም ሊከላከሉት የሚችሉ ነገር ግን በአለም ላይ ለብዙዎች የሞት መንስኤ የሆነ ነው ብለዋል ፡፡
ምንጭ ፡ሮይተርስ