Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ሼህ ኑሩ ይማምን በሽጉጥ ገድለዋል በሚል የተከሰሰሱት ግለሰቦች ጥፋተኛ ተባሉ

0 935

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ሼህ ኑሩ ይማምን በሽጉጥ ገድለዋል በሚል የተከሰሰሱት ግለሰቦች ጥፋተኛ ተባሉ

ሼህ ኑሩ ይማምን በሽጉጥ ገድለዋል በሚል የተከሰሰሱት ግለሰቦች ጥፋተኛ ተባሉ

በደሴ ከተማ የሸዋ በር መስጅድ የሃይማኖት አባት የሆኑት ሼህ ኑሩ ይማምን በሽጉጥ በመምታት ህይወታቸው እንድያልፍ በማድረግ የተከሰሰሱት ግለሰቦች ጥፋተኛ ተብለዋል።

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ በዋለው ችሎት 13ቱ ተከሳሾች እስላማዊ መንግስት ለመመስረት እና አላማቸውን የማይደግፍ አካላት ላይ የሃይል እርምጃ ለመወሰድ ሲቀሳቀሱ ነበር ተብለው በተመሰረተባቸው የሽብር ወንጀል ክስ ጥፋተኛ ናቸው ሲል ብይን ሰጥቷል።

ጥፋተኛ የተባሉት ተከሳሾች 1ኛ አህመድ እንድሪስ፣ 2ኛ አንዋር ኡመር፣ 3ኛ ሷሊህ መሃመድ፣ 4ኛ አደም አረጋውያን ጨምሮ አስራ ሶስት ተከሳሾች ናቸው።

የአቃቤ ህግ ክስ እንደሚያመላክተው ተከሳሾቹ ከ2004 ዓ.ም ጀምሮ አክራሪነትን ለማስፋፋት በመደራጀት እስላማዊ መንግስት ለመመስረት ተቀሳቅሰዋል።

በሰኔ 27 ቀን 2005 ከምሽቱ 2 ስዓት በደሴ ከተማ የሸዋ በር መስጅድ የሃይማኖት አባት የሆኑት ሼህ ኑር ይማምን በሽጉጥ ግንባራቸው ላይ ሁለት ጊዜ በመምታት መግደላቸውም በክሱ ላይ ተመላክቷል።

በተለያዩ ጊዜያትም የእነሱን አላማ የማይደግፉ ግለሰቦች ላይ የሃይል እርምጃ ለመውሰድ ተቀሳቅሰዋል ይላል አቃቤ ህግ በክሱ።

የግራ ቀኙን ክርክር አዳምጦ ተከሳሾቹን ጥፋተኛ ያለው የልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት የቅጣት ውሳኔ ለመወሰን ለጥር 9 ቀን 2009 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy