Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በመድሃኒት በሚላመዱ ባክቴሪያዎች ላይ የሚያደርጉት ጥናት ውጤታማ ደረጃ ላይ መድረሱን ተመራማሪዎች አስታወቁ

0 677

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

መድሃኒት በሚላመዱ ባክቴሪያዎች ላይ የሚያደርጉት ጥናት ውጤታማ ደረጃ ላይ መድረሱን ተመራማሪዎች አስታወቁ፡፡

ተመራማሪዎቹ ይፋ እንዳደረጉት  መድሃኒት የሚለማመዱ  ባክቴሪያዎችን  የመቋቋም  ሃይል ያላቸውን ሞለኪዮሎች በማበልፀግ በባክቴሪያ የሚተላለፉ በሽታዎችን ለመቋቋም የሚያስችል በር ከፋች  ደረጃ ላይ መድረሳቸውን  ተናግረዋል፡፡

ተመራማሪቹ  ያበለፀጉት ግኝት ፀረ ባክቴሪያ መድሃኒቶችን  የተለማመዱ  ባክቴሪያዎችን  በመቋቋም የተሸለ ውጤት የሚያመጡ መድሃኒቶችን  ለመስራት በር የሚከፍት መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት  በ2014 ባወጣው ትምበያ  መሰረት እ ኤ አ በ2050 መድሃኒት በሚለማዱ ባክቴሪያ በሚመጡ በሽታዎች  ሳቢያ 300 ሚሊዮን  የሚሆኑ ሰዎች  ሊሞቱ እንደሚችሉና ይህም  ከፍተኛ ስጋት የሚፈጥር ጉዳይ መሆኑን የተባባሩት መንግስታት  ድርጅት  ገልጿል፡፡

በተላላፊ ባክቴሪያ  የሚከሰቱ እንደ ሳምባ ምች( pneumonia) የአንጀት ኢንፌክሽን( E. coli) እና እንደ  አባለዘር በሽታዎች  ያሉ  በቀላሉ  በቁጥጥር ስር ሊዉሉ የሚችሉ በሽታዎች  በአሁኑ ሰአት  በፍጥነት እየተስፋፉና ፀረ ባክቴሪያ  መድሃኒቶችን  እየተለማዱ መሆኑን  ተመራማሪዎቹ ገልጸዋል፡፡

በቀጣይም  አዳዲስ መድሃኒቶችን ይዘው ለመቅረብ  በፍጥነት  መንቀሳቀስ እንደሚያስፈልግና የአሁኑ ግኝታቸውም በር ከፋች መሆኑን ተመራማሪዎቹ  አስታውቀዋል፡፡

ምንጭ ፡ሳይቲስት አለርት

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy