Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ጉዳዮች ላይ የሚመክረውን የዓለም ኢኮኖሚ ፎረም ለማስተናገድ ጥያቄ አቀረበች

0 427

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ጉዳዮች ላይ የሚመክረውን የዓለም ኢኮኖሚ ፎረም ለማስተናገድ ጥያቄ አቀረበች

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ጉዳዮች ላይ የሚመክረውን የዓለም ኢኮኖሚ ፎረም ለማስተናገድ ጥያቄ አቀረበች

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ጉዳዮች ላይ የሚመክረውን የዓለም ኢኮኖሚ ፎረም ለማስተናገድ በይፋ ጥያቄ አቀረበች።

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም በዳቮስ ስዊዘርላንድ ከዓለም ኢኮኖሚ ፎረም መስራችና ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፕሮፌሰር ክላውስ ማርቲን ሽዋብ ጋር ተነጋግረዋል።

በዚሁ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም እንደገለጹት፥ ኢትዮጵያ ከዓለም የኢኮኖሚ ፎረም ጋር ያላት ስትራቴጂያዊ ግንኙነት አጠናክራ ትቀጥላለች።

ይህን ግንኙነቷን ለማጎልበትም እ.ኤ.አ በ2018 በአፍሪካ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ሰጥቶ የሚመክረውን የዓለም ኢኮኖሚ ፎረምን ለማስተናገድ በይፋ ጥያቄ አቅርበዋል።

ቀደም ሲል ኢትዮጵያ የዓለም ኢኮኖሚ ፎረምን “የአፍሪካን መዋቅራዊ ሽግግር መልክ ማስያዝ” በሚል ጭብጥ በ2012 በአዲስ አበባ በብቃት ማስተናገዷን አውስተዋል።

ፕሮፌሰር ክላውስ ሽዋብ በበኩላቸው፥ ኢትዮጵያ እያስመዘገበች ያለውን ፈጣን ኢኮኖሚያዊ ዕድገት የዓለም ኢኮኖሚ ፎረም በቅርበት እየተከታተለው መሆኑን ተናግረዋል።

ሃገሪቱ እያስመዘገበች ያለው ፈጣን ዕድገት ለሌሎች ታዳጊ ሃገራት በዓርአያነት የሚጠቀስ እንደሆነም ነው የተናገሩት።

ኢትዮጵያ ያቀረበቸው ጥያቄ በደቡብ አፍሪካ ደርባን በሚካሄደው ስብሰባ በፎረሙ የአሰራር ስርዓት መሰረት ምላሽ እንደሚያገኝ ገልጸዋል።

በተለይ ኢትዮጵያ ዓለም አቀፋዊና አሕጉራዊ ጉባዔዎችን በማስተናገድ በኩል ያላት ብቃትና ዝግጁነት ፎረሙን እንድታዘጋጅ ሊያስመርጣት እንደሚችል ነው ፍንጭ የሰጡት።

በተመሳሳይ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ከማይክሮሶፍት መሥራችና ባለቤት ከቢሊየነሩ ቢል ጌትስ ጋር በዳቮስ ምክክር አካሂደዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት፥ ኢትዮጵያ በአዲስ አበባ የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ወይም አይ.ቲ ፓርክ እያቋቋመች መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህም ወጣቶችን ተጠቃሚ በሚያደርገው ፓርክ የማይክሮሶፍት ተሳትፎና ድጋፍ አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል።

ባለሀብቱ ቢል ጌትስም ለአዲስ አበባ አይ.ቲ ፓርክ ድጋፍ እንደሚያደርጉ መናገራቸውን ውይይቱን የተከታተሉት በስዊዝርላንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር ነጋሽ ክብረት አስረድተዋል።

እንደ ኢዜአ ዘገባ ቢልና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን እኤአ በ2012 ጽህፈት ቤቱን በአዲስ አበባ ከፍቶ በመስራት ላይ ይገኛል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy