Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ኦሮሚያ ክልል ለ10 ሺህ የህግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ

0 431

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የኦሮሚያ ክልል ለ10 ሺህ የህግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ

የኦሮሚያ ክልል ለ10 ሺህ የህግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ

የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ለ10 ሺህ የህግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ።

በማረሚያ ቤት ቆይታቸው መልካም ስነ ምግባር ያሳዩና ወደ ህብረተሰቡም ሲቀላቀሉ ለውጥ ማምጣት ይችላሉ ተብሎ የታመነባቸው ታራሚዎች ናቸው ይቅርታ የተደረገላቸው።

ታራሚዎቹ በክልሉ ህገ መንግስት አንቀፅ 57(3) (1) መሰረት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ይቅርታ እንደሚያደርግ በሚደነግገው መሰረት የተለቀቁ መሆናቸውም ተጠቁሟል።

በይቅርታ ከተለቀቁት የህግ ታራሚዎች መካከል የእድሜ ልክ ጽኑ እስራት ተፈርዶባቸው 13 ዓመት እና ከዚያ በላይ በእስር ላይ የነበሩ ይገኙበታል።

ከስድስት ወር እስከ 25 ዓመት የሚደርስ ጽኑ እስራት ተፈርዶባቸው አንድ ሶስተኛውን የእስር ጊዜ ያጠናቀቁ ታራሚዎችም ይቅርታ ከተደረገላቸው ውስጥ እንደሚገኙ ተገልጿል።

የኢፌዴሪ እና የኦሮሚያ ክልል ህገ መንግስት አንቀፅ 28 ተላለፈው ወንጀል የፈጸሙ፣ የሞት ፍርድ የተፈረደባቸው፣ ከዚህ በፊት በይቅርታ ተለቀው ሌላ ወንጀል በመስራት ዳግም ለእስር የተዳረጉ፣ በሙስና ወንጀል ተፈርዶባቸው በእስር ላይ የሚገኙ፣ አስገድዶ መድፈር እና የተለያዩ ጾታዊ ጥቃት የፈጸሙ እንዲሁም በህገ ወጥ የሰዎች ዝወውር ወንጀል የታሰሩ ሰዎች በይቅርታው አልተካተቱም።

ይቅርታ የተደረገላቸው የህግ ታራሚዎች ከዚህ ቀደም ካጠፉት ጥፋት በመማር ወደ ህብረተሰቡ በሚቀላቀሉበት ጊዜ በማረሚያ ቤት ባገኙት እውቀትና መልካም ስነ ምግባር የልማት ሀይል ይሆናሉ ተብሎ እንደታመነባቸውም የክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ አመልክቷል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy