Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ኮሚሽኑ በድርቅ ለተጎዱ አካባቢዎች አስቸኳይ የሰብዓዊ ድጋፍ እያደረገ ነው

0 1,183

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ኮሚሽኑ በድርቅ ለተጎዱ አካባቢዎች አስቸኳይ የሰብዓዊ ድጋፍ እያደረገ ነው

ኮሚሽኑ በድርቅ ለተጎዱ አካባቢዎች አስቸኳይ የሰብዓዊ ድጋፍ እያደረገ ነው

ብሄራዊ የአደጋ ሥጋት አመራር ኮሚሽን ከክልል መንግሥታት ጋር በመተባበር በድርቅ ለተጎዱ አካባቢዎች አስቸኳይ የሰብዓዊ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን አስታወቀ።

ኮሚሽኑ በድርቅ በተጎዱ አካባቢዎች ለእንስሳት መኖ እያቀረበ መሆኑንም ገልጿል።

ኮሚሽነሩ አቶ ምትኩ ካሳ ለኢዜአ እንደገለጹት፥ 5 ነጥብ 6 ሚሊየን ለድርቅ ተጋላጭ የሆኑ ዜጎችን ለመታደግ መንግሥት ሰብዓዊ ድጋፍ እያቀረበ ነው።

መጪውን ሁለት የበጋ ወራት ግምት ውስጥ በማስገባትም መንግሥት በድርቅ በተጠቁ አካባቢዎች ለሚኖሩ ዜጎች የምግብና የቁሳቁስ ድጋፍ ከወዲሁ ለማድረግ ተዘጋጅቷል ብለዋል።

አሁን የድርቅ አደጋው የሚስተዋለው አርብቶ አደር በሚኖርባቸው የደቡብ ምሥራቅ የሃገሪቱ አካባቢዎች እንደሆነም ኮሚሽነር ምትኩ ተናግረዋል።

ከዓሳና እንስሳት ኃብት ልማት ሚኒስቴርና ከክልል ቢሮዎች የተውጣጣ የእንስሳት ህክምና ቡድንም ድርቅ ባጠቃቸው አካባቢዎች ተሰማርቶ የህክምና አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን አስረድተዋል።

በእስካሁኑ ሂደትም 148 ሺህ እስር የእንስሳት መኖ ከፌደራልና ከክልል መንግስታት ለደቡብ ኦሞ ዞን ማድረስ የተቻለ ሲሆን፥ አምስት የንጹህ መጠጥ ውኃ ማጠራቀሚያ ታንከሮችም በመሰራት ላይ እንደሆኑ ጠቁመዋል።

በተመሳሳይ ለኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል 50 ሺህ እስር የእንስሳት መኖ እንዲሁም 10 ሺህ ኩንታል አልሚ ምግብ በድርቁ ለተጠቁ ዜጎች ድጋፍ ተደርጓል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy