Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የአፋርና አማራ ክልል የጋራ የልማት ትብብር መድረክ ዛሬ በሰመራ ከተማ ተካሄደ

0 1,152

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የአፋርና አማራ ክልል የጋራ የልማት ትብብር መድረክ ዛሬ በሰመራ ከተማ ተካሄደ

የአፋርና አማራ ክልል የጋራ የልማት ትብብር መድረክ ዛሬ በሰመራ ከተማ ተካሄደ

ሰመራ ታህሳስ 23/2009 ክልሉ እያስመዘገበ ያለውን ሁለንተናዊ እድገት ለማስቀጠል ከአጎራባች ክልሎች ጋር ያላቸውን የልማት ትብብር አጠናክረው እንደሚቀጥሉ የአፋር ክልል ርእሰ መስተዳድር አስታወቁ፡፡

የአፋርና አማራ ክልል የጋራ የልማት ትብብር መድረክ ዛሬ በሰመራ ከተማ ተካሄዷል፡፡

መድረኩን በንግግር የከፈቱት የአፋር ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ስዩም አወል እንደተናገሩት የክልሉ መንግስት ባለፉት ሁለት አስርት አመታት አርብቶ አደሩን በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚዊና ፖለቲካዊ መስኮች ተሳታፊና ተጠቃሚ ከማድረግ አኳያ አበረታች ውጤት ተመዝግቧል፡፡

ለተመዘገቡት ስኬቶች የፌዴራል መንግስት ድጋፍና የአጎራባች ክልሎች ጋራ የልማት ትብብር ቁልፍ ሚና መጫወቱን ገልጸዋል፡፡

”ከአጎራባች ክልሎች ጋር የልማት ትስሰሩን ከማጠናከር ባለፈ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትና ትስስሩን በማጎልበት ሃገሪቱ አንድ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ማህበረሰብ ለመገንባት የጀመረችው ጥረት ወደላቀ ደረጃ እንዲሸጋገር ያስችላል” ብለዋል፡፡

በመሆኑም ክልሉ ያስመዘገበው አርብቶ አደሩን ተጠቃሚ ያደረገ ሁለንተናዊ እድገት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ከአጎራባች ክልሎች ጋር የተጀመረውን የጋራ የልማት ትብብር ለማሳደግ የበለጠ ተቀራርቦ እንደሚሰራ ገልፀዋል፡፡

የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በውይይቱ ማጠቃለያ ላይ እንደተናገሩት የሁለቱ ክልል ህዝቦች የቆየ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ያላቸው በመሆኑ የልማት ትብብሩ ይህን ወደላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግር ተናግረዋል፡፡

ሁለቱ ክልሎች በተለይ በአስተዳደርና ጸጥታ ዘርፉ በበለጠ ተቀራርበው በመስራታቸው ከዚህ በፊት ከወሰንና የሃብት አጠቃቀም ጋር ተያይዞ ይነሱ የነበሩ ግጭቶች በከፍተኛ መጠን መቀነስ መቻሉን ገልፀዋል፡፡

በመሆኑም ”ለልማት እቅዱ ተፈጻሚነት በሁሉም ዘርፍ በሚፈለገው ደረጃ ተግባራዊ በማድረግ የሁለቱን ክልል አጎራባች ህዝቦች ተጠቃሚ ለማድረግ እንቅፋት የሆኑ የአሰራር ክፍተቶችን በማረም እቅዱን ወጥነት ባለው አግባብ ተግባራዊ ማድረግ ይገባል” ብለዋል፡፡

ለዚህም የሁለቱ ክልል አመራሮች የጋራ ልማት ትብብር ስራውን ከፍተኛ ትኩረት ሰጥተው ሊመሩት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

የአፋር ክልል ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማን መቅቡል በበኩላቸው ክልሉ ያለበትን የአቅም ክፍተት ለመሙላት የጋራ የልማት ትብብሩ ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከዚህ አንጻር የአማራ ክልል ከ1989 ዓ.ም ጀምሮ የአፋር ክልል ያለበትን የማስፈጸም አቅም ውስንነት ለመፍታት የቴክኒክና በተመረጡ ዘርፎች ደግሞ የአቅም ግንበታ ድጋፍና የልምድ ልውውጥ በማድረግ የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በዚህም  በትምህርትና ጤና እንዲሀም በአስተዳደርና ጸጥታ ሴክተሮች የተሻለ አፈጻጸም የታየ ሲሆን ይህም በሌሎች ዘርፎች ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሁሉም ባለድርሻ አካላት ንቁ ተሳትፎ ሊያደርጉ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

በጋራ የልማት ትብብር መድረኩ ላይ የሁለቱ ክልል ከፍተኛ አመራሮችና ባለሙያዎች የተገኙ ሲሆን በተጣዩ ግማሽ ዓመት እቅድ ላይ የሁለቱ ክልል ርእሰ መስተዳድሮች የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy