Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ባለስልጣን የመረጃ ተደራሽነቱን ክፍተት እንዲፈታ ምክር ቤቱ አሳሰበ

0 2,939

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ባለስልጣን የመረጃ ተደራሽነትን ለማረጋገጥና በዋጋ ማሣያ ሠሌዳዎች ዙሪያ የሚታየውን ከፍተት ለመፍታት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እንዲሰራ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የንግድ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አሳሰበ፡፡

ቁሚ ኮሚቴው የባለስልጣኑን የ2ዐዐ9 በጀት ዓመት የስድስት ወራት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ገምግሟል፡፡

ባለስልጣኑ በጥናትና የገበያ መረጃ ትንትና ግልፅነት እንዲሁም ፍትሃዊና ውድድር የሠፈነበት የግብይት ሥርአትን ማከናወን መቻሉ ኮሚቴው በጥንካሬ ተመልክቷል፡፡

ተቋሙን አሠራር ውጤታማና ቀልጣፋ ለማድረግ አሠራሩን በመፈተሽ በማሻሻል በኩልም ቋሚ ኮሚቴው በጥንካሬ አንስቷል፡፡

በሌላ በኩል የምርት ገበያ መረጃ ተደራሽነትንና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በተለያዩ አካባቢዎች በቀጥታ ሥርጭት የሚተላለፋባቸው የዋጋ ማሳያ ሰሌዳዎች ተገቢውን አገልግሎት እየሠጡ አለመሆናቸው ቋማ ኮሚቴው በእጥረት ገምግሟል፡፡

በህብረት ሥራ ማህበራት ጋር ቅንጅታዊ ሥራውን አጠናክሮ አለመቀጠሉንም ቋሚ ኮሚቴው ገምግሟ ፡፡

መስሪያ ቤቱ የግብይት አፈፃፀመን ዘመናዊ ለማድረግና የገበያ ደህንነትን ለመጠበቅ አመራሩ ቁርጠኛ ሆኖ መምራት እንዳለበት የንግድ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሰቢ አቶ ዘውዱ ከበደ አሳሰበዋል፡፡

የምርት ገበያ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ኩሌሮ ኡፒዱ በበኩላቸው ቋሚ ኮሚቴው ያያቸውን ክፍተቶች በማረም የግብይት ሥርአቱን ዘመናዊ ለማድረግና ለማሻሻል ደንቦችና መመሪያዎችን እያዘጋጀ መሆኑን ጠቅሰው፣ የላቀ ግብአት ሥርአት እንዲኖር ልዩ ትኩረት ሠጥተው እንደሚሠሩ ገልፀዋል፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy