Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የኢትዮ-ጂቡቲ የባቡር መስመር መገንባት የሁለቱ አገራት ማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ ትስስር ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግረው ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ገለጹ።

0 446

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የኢትዮ-ጂቡቲ የባቡር መስመር መገንባት የሁለቱ አገራት ማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ ትስስር ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግረው ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ገለጹ።
ከኢትዮጵያ ድንበር እስከ ጂቡቲ ድረስ የሚዘልቀው የባቡር መስመር ዛሬ ተመርቋል።
የአንድ መቶ አመት ታሪክ ያለው የኢትዮ-ጂቡቲ የባቡር መስመር የሁለቱን አገራት ሁለንተናዊ ዕድገት በሚያመጣ መልኩ ተገንብቶ ተመርቋል።
በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ የተገኙት የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ እንዳሉት የኢትዮ-ጂቡቲ የባቡር መስመር ሁለቱ አገራት ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት በማስመዝገብ ግንኙነታቸውን ወደ ላቀ ደረጃ ያሳድገዋል።
የባቡር መስመሩ መገንባት ወደ መሀል አገር ሸቀጦችን በተሽከርካሪ ለማድረስ ይወስድ የነበረውን የስድስት ቀናት ጉዞ ወደ አንድ ቀን በመቀነስ የትራንስፖርት አቅምን ያሳድጋልም ብለዋል።
የጠቅላይ ሚንስትሩ ልዩ አማካሪ አምባሳደር ብርሀነ ገብረክርስቶስ የባቡር መስመሩ ዝርጋታ በሀምሳ ዓመታት ውስጥ አህጉረ አፍሪካን በባቡር ለማስተሳሰር የተያዘውን እቅድ አካል ነው ብለዋል።
ጠቅላይ ሚንስትሩ ከ750 ኪሎሜትር በላይ ርዝመት ያለው የኢትዮ ጂቡቲ የባቡር መስመር አገሪቱ ለጀመረችው የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግር አይነተኛ ሚና እንደሚጫወትም ተናግረዋል።
የጂቡቲው ፕሬዝዳንት ኢስማእኤል ኡመር ጊሌ በበኩላቸው የባቡር መስመር ግንባታው የሁለቱን አገራት ታሪካዊ ግንኙነት ይበልጥ የሚያጠናክር፣ የስራ ዕድልና የሀብት ክምችት እንደሚፈጥርም አመልክተዋል።
ሪፖርተር:-ጌታቸው ጫኔ

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy