Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ድህነትና ርሃብን ከገፀ ምድር ለማስወገድ 265 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ ተመድ ገለፀ

0 385

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የዘላቂ ልማት ግቦች አካል የሆኑትን ድህነትና  ርሃብን ከገፀ  ምድር ለማስወገድ 265 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ገለፀ።

በሮም እየተካሄደ ባለ የድርጅቱ ጉባኤ ላይ እንደተገለፅው ድህናትንና ርሃብን   እስከ 2030 ለማሸነፍ የተያዘው ግብ እንዲሳካ ካስፈለገ አለም የሚያስፈልገውን በጀት ብፍጥነት ዝግጁ  ሊያደርግ ይገባል።

በተመድ የግብርና ልማት አለም አቀፍ ፈንድ ፕሬዝዳንት ካናዮ ንዋዜ በጉባኤው መክፈቻ ላይ እንዳሉት የታቀዱትን ሁለቱን ግቦች ለማሳካት 265 ቢሊዮን ዶላሩን ማፈላለግ ጊዜ  የማይሰጠው  ጉዳይ ነው።

ሀላፊው እንዳሉት ድህነትና ርሃብን ለማጥፋት በርካታ ጥረት ቢደረግም ህፃናትን ጨምሮ   800 ሚሊዮን ሰዎች በየቀኑ የርሃብ ገፈት ቀማሾች ናቸው።ከዚሁ  ቁጥር የማይተናነሱት ደግሞ ከድህነት ወለል በታች ይኖራሉም ብለዋል።

ፈንዱን ለማሰባሰብም  የተለያዩ  ፈጥራዎችን ተግባር ላይ ማዋል እንደሚጠይቅም በጉባኤው ተመልክቷል።

ፕሬዝዳንቱ የግል ዘርፉንና በጎ  አድራጊዎችን   በገጠሩ አካባቢ  ግብርና ላይ ሀብታቸውን እንዲያፈሱ  በማድረግም ችግሩን መቀነስ  እንደሚቻልም አመልክተዋል።

የመደረኩ ተካፋዮችም ችግሩን በመንግስታት  ጥረት ብቻ ማስወገድ እንደማይቻል በማመን  የቀረቡት አማራጮች ላይ ትኩርት እንዲደርግ መስማማታቸውን  የተመድ  ዘገባ ያስረዳል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy