Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ድርጅቱ በምሥጢራዊ የህትመት አገልግሎት አሰጣጥ ተወዳዳሪ ለመሆን መስራት አለበት: – ፕ/ት ሙላቱ ተሾመ

0 501

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የብርሃንና ስላም ማተሚያ ድርጅት በመደበኛና በምሥጢራዊ የህትመት አገልግሎት አሰጣጥ ተወዳዳሪ ለመሆን በዘርፉ የቴክኖሎጂ አካዳሚ ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንዳለበት ፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመ ገለጹ።

የድርጅቱ ዘጠና አምስተኛ ዓመት የምስረታ በዓል  ሲያከብር አዲስ ያስገነባውን የህትመት ቴክኖሎጂ አካዳሚ እና የማስፋፊያ ፕሮጀክት አስመርቋል።

ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ  በወቅቱ እንደገለጹት፤ በመደበኛና በምሥጢራዊ የህትመት አገልግሎት ተወዳዳሪ ለመሆን መስራት ይጠበቅበታል።

ድርጅቱ በህትመት ዘርፍ የተሻለ ኢንዱስትሪ እንዲሆን መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርገ ተናግረዋል።

የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተካ አባዲ በበኩላቸው፤ አካዳሚው የድርጅትን የውስጥ ችግር ከማቃለል ባሻገር ለአገሪቷ ማተሚያ ቤቶችና ለምስራቅ አፍሪካ አገሮች የሥልጠና ማዕከል ሆኖ ያገለግላል።

ድርጅቱ ትላንት ላስመረቃቸው የማስፋፊያ ፕሮጀክቶች ከስድስት መቶ ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ማድረጉን ኢዜአ ዘግቧል።

ለረጅም ዓመታት የድርጅቱ ደንበኛ ለሆኑ መስሪያ ቤቶችና ከፍተኛ አስተዋጽዖ ላበረከቱ የድርጅቱ ሰራተኞች ሽልማት አበርክቷል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy