Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ጠ/ሚ ኃይለማርያም በአዲሱ የጋና ፕሬዚዳንት በዓለ ሲመት ላይ ታደሙ

0 377

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ጠ/ሚ ኃይለማርያም በአዲሱ የጋና ፕሬዚዳንት በዓለ ሲመት ላይ ታደሙ

ጠ/ሚ ኃይለማርያም በአዲሱ የጋና ፕሬዚዳንት በዓለ ሲመት ላይ ታደሙ

አዲሱ የጋና ፕሬዚዳንት ናና አኩፎ አዶ ቃለ መሀላ ፈፀሙ።

በፕሬዚዳንቱ በዓለ ሲመት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝንን ጨምሮ የ11 የአፍሪካ ሀገራት መሪዎችና ከ6 ሺህ በላይ እንግዶች ተገኝተዋል።

የ72 አመቱ የቀድሞ የሰብአዊ መብት ጠበቃ ናና አኩፎ አዶ በመዲናዋ አክራ ነው ቃለ መሀላ የፈፀሙት።

ፕሬዝዳንት ናና አኩፎ አዶ ባለፈው ታህሳስ በተካሄደው ሀገራዊ ምርጫ 53 ነጥብ 8 በመቶ ድምጽ በማግኘት ማሸነፋቸውን የሚታወስ ነው።

የተቃዋሚ የዓርበኞች አዲስ ፓርቲን ወክለው የተወዳደሩት አዶ በፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የአሁኑን ጨምሮ ለሦስተኛ ጊዜ በመወዳደር ነው ዘንድሮ ማሸነፍ የቻሉት።

“ለለውጥ ዝግጁ ናቸው” ተብሎ የሚነገርላቸው የ72 ዓመቱ ተመራጭ ፕሬዝዳንት አኩፎ አዶ ምርጫውን ያሸነፉት የአገሪቷን ዴሞክራሲያዊ ሂደት ባመላከተ ጠንካራ ፉክክር ነው።

በምርጫውም የብሔራዊ ዴሞክራቲክ ኮንግረስ ፓርቲ ተወካይና የአገሪቱን ፕሬዝዳንት ጆን ድራማኒ ማህማን ማሸነፍ ችለዋል።

በሰብዓዊ መብት ጠበቃነታቸው የሚታወቁት ተመራጩ ፕሬዚዳንት አዶ ኩፎር በፕሬዝዳንት ማሃማ የሥልጣን ዘመን “ወድቋል” የሚባለውን የጋና ኢኮኖሚ እንዲያንሰራራ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።

የጋና ኢኮኖሚ መውደቅ እንዲሁም ለአገሪቱና ለውጪ ባኃብቶች አመቺ ያለመሆን በምርጫ የተሸነፉትን ፕሬዝዳንት ማሃማን አጣብቂኝ ውስጥ ከቷቸው ነበር።

በወቅቱ የጋና ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት ጆን ማህማ በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩትን የአገሪቱ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ጆን ኢቫንስ አታ ሚልስን ተክተው ነበር እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ 2012 ወደ ሥልጣን የመጡት።

ጆን ማህማ በወቅቱ በፈጣን ዕድገት ላይ የነበረውን የጋና ኢኮኖሚ ያስቀጥላሉ ተብሎ ተስፋ የተጣለባቸው ቢሆንም አፈፃጸሙ ግን ከግምት ውጭ ሆኗል።

በእርሳቸው ዘመን በጋና የኃይል አቅርቦት እጥረት እየከፋ መምጣቱ ነው የሚገለጸው።

በታህሳስ በተካሄደው ምርጫ ሕዝቡ ድምጹን የሰጣቸው አዲሱ ፕሬዝዳንት ጋና ካጋጠማት ኢኮኖሚያዊ ድቀት እንደሚታደጓት ይታመናል።

ጋና እንደ አወሮፓውያን አቆጣጠር ከ1992 ጀምሮ ወደ ብዝሃ ፓርቲ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ከተሸጋገረች በኋላ በምዕራብ አፍሪካ የተረጋጋች አገር መሆኗ ይነገርላታል።

አዲሱ ፕሬዚዳንት ናና አኩፎ አዶ በጋና ከ200 በላይ በሚሆኑ ወረዳዎች ፋብሪካዎችን ለመገንባት እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርትን በነፃ እንዲሰጥ አደርጋለሁ በማለት ቃል መግባታቸው ይታወሳል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy