Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ምርት ገበያው በስድስት ወራት 246 ሺህ ሜትሪክ ቶን ምርት አገበያየ

0 951

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ምርት ገበያው በስድስት ወራት 246 ሺህ ሜትሪክ ቶን ምርት አገበያየ

 

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ በ2009 በጀት ዓመት በመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት 10 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር ዋጋ ያለው ከ246 ሺህ በላይ ሜትሪክ ቶን ምርት ማገበያየቱን አስታወቀ።

ምርት ገበያው ቡና፣ ነጭ ቦሎቄ፣ ሰሊጥ፣ በቆሎ፣ ስንዴ፣ ማሾና ቀይ ቦሎቄ በማገበያየት ላይ የሚገኝ ሲሆን በስድስት ወራት ውስጥ የተገኘው ውጤት ከእቅዱ ጋር ሲነጻጸር የምርት ግብይቱ 96 በመቶ፣ የምርት ዋጋውን ደግሞ 94 በመቶ አሳክቷል፡፡

ይህ አፈጻጸም ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲነጻጸር አጠቃላይ የምርት ግብይት መጠን
ስድስት በመቶ ቢቀንስም የቡና ግብይት መጠን በ15 በመቶ፣ የነጭ ቦሎቄ ደግሞ በ23 በመቶ መጨመሩንም ምርት ገበያው ገልጿል።

የምርት ግብይት ዋጋ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲጻጸር በ19 በመቶ ብልጫ እንዳለውም ነው የጠቆመው።

ከዚህ ውስጥ የቡና ግብይት ዋጋ በ35 በመቶ፤ የነጭ ቦሎቄ የግብይት ዋጋ በ82 በመቶ እድገት ያሳዩ ሲሆን ሰሊጥ በ14 በመቶ ቅናሽ አስመዝግቧል።

ምርት ገበያው ከድምፅ ማስተጋባት ግብይት ወደ ዘመናዊው ኤሌክትሮኒክ ግብይት ከ18 ወራት በፊት
ያደረገው ሽግግር ለተገኘው ውጤት አስተዋጽኦ ማድረጉን አስታውቋል።

ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ አጠቃላይ የኤሌክትሮኒክ የምርት ግብይት መጠን 89 በመቶ ደርሷል፡፡

ምርት ገበያው የሚሰጠውን ዘመናዊ የግብይት አሰራር በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች ተደራሽ ለማድረግ ሰባት
የግብይት ማዕከላትን ለማቋቋም ያቀደ ሲሆን፥ በ2009 በጀት ዓመት በሀዋሳ፣ ነቀምትና ሁመራ እየተገነቡ የሚገኙትን ማዕከላት ሥራ ለማስጀመር ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል።

ከጥቂት ወራት በኋላ ሀዋሳ የሚገኘው የኤሌክትሮኒክ የግብይት ማዕከል በይፋ ተመርቆ ሥራ የሚጀምር ይሆናል።

ተጨማሪ አራት የኤሌክትሮኒክ ግብይት ማዕከላትን በጂማ፣ አዳማ፣ ጎንደርና ኮምቦልቻ ከተሞች ለማስገንባት እየሰራ እንደሚገኝም ምርት ገበያው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ አመላክቷል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy