Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ሞሮኮ ወደ አፍሪካ ህብረት ለመቀላቀል ያቀረበችው ጥያቄ ሰኞ ውሳኔ ይሰጥበታል

0 1,613

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ሞሮኮ ዳግም ወደ አፍሪካ ኅብረት ለመቀላቀል ያቀረበችው ጥያቄ ሰኞ በሚካሄደው የህብረቱ የመሪዎች ጉባኤ ውሳኔ ይሰጥበታል።

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር ንኮሳዛና ድላሚኒ ዙማ በሞሮኮ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳላሄዲኔ ሜዟር የተመራውን የልዑካን ቡድን ተቀብለው አነጋግረዋል።

በውይይታቸውም ሞሮኮ ከአፍሪካ ህብረት መቋቋሚያ ሕገ-ደንብና ከህብረቱ ጋር አብራ ልትሄድ በሚቻልበት ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

ሊቀ-መንበሯ ለቡድኑ ሞሮኮ ወደ አፍሪካ ህብረት ዳግም እንድትቀላቀል ለማስቻል በሕገ-ደንቡ ጥያቄዋ እየታየላት መሆኑን ገልጸዋላቸዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ሰኞ በሚካሄደው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለውይይት የሚቀርብ አጀንዳ መሆኑን ነው ያረጋገጡት።

ጉባኤው ሲጠናቀቅም ውሳኔው ለሞሮኮ ወዲያውኑ ይፋ እንደሚደረግ ሊቀ-መንበሯ አረጋግጠዋል።

ሞሮኮ የቀድሞ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት መስራች አገር ብትሆንም ድርጅቱ ለዓረብ ሰሃራዊት አባልነት ሲሰጥ የድርጅቱን እርምጃ በመቃወም ራሷን በይፋ ማግለሏ ይታወሳል።

ሞሮኮ ከኅብረቱ ከወጣች ከ32 ዓመታት በኋላ የአፍሪካ ኅብረትን የመተዳደሪያ ደንብ አከብራለሁ፤ ዳግም ወደ ኅብረቱ ለመቀላቀል እፈልጋለሁ በማለት ይፋዊ ጥያቄ አቅርባለች።

ጥያቄው ለኅብረቱ የቀረበው በአሜሪካ ኒውዮርክ በተካሄደው 71ኛው የመንግሥታቱ ድርጅት ጉባኤ ላይ በሞሮኮው ንጉሥ መሐመድ ስድስተኛ የውጭ ጉዳይ አማካሪ ታይብ ፋሲ ፊህሪ አማካኝነት ነበር።

ለህብረቱ የቀረበውን ጥያቄ የኮሚሽኑ ሊቀ-መንበር ድላሚኒ ዙማ መቀበላቸው ይታወቃል።

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy