Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ሲጋራ በማጨስ በየአመቱ አለም 1 ትሪሊዮን ዶላር እንደምታጣ የአለም ጤና ድርጅት አስታወቀ

0 832

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ሲጋራ በማጨስ በየአመቱ አለም 1 ትሪሊዮን ዶላር እንደምታጣ የአለም ጤና ድርጅት  አስታወቀ፡፡

የአለም ጤና ድርጅት  ባካሄደው  ጥናት የሲጋራ አጫሾች ቁጥር በማሻቀብ ላይ  መሆኑን ጠቅሶ ፣ይህም የአለም  ስጋት

እየሆነ መምጣቱን አመልከቷል፡፡

አዲሱ ጥናት እንዳመለከተው በሚቀጥሉት አመታት ከማጨስ ጋር በተያያዘ  የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር መጨመሩንም አሳይቷል፡፡

በአሁን ሰአት በአለም ላይ  ከሲጋራ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ  ስድስት ሚሊዮን ሰዎች  በየአመቱ እንደሚሞቱ ያሰቀመጠው  ጥናቱ፣ ይህ ቁጥር ግን እኤአ በ2030  እስከ 8 ሚሊዮን ከፍ  ሊል እንደሚችል  የአለም ጤና ድርጅት ስጋቱን ገልጿል፡፡

ከማጨስ ጋር  በተያያዘ በምርታማነት ደረጃና በጤና አገልግሎት ላይ ከሚከሰቱ አሉታዊ  ምክንያቶች የተነሳ በየአመቱ ቢያንስ  እስከ 1 ትሪሊየን ዶላር  በአለም ኢኮኖሚ ላይ ኪሳራ  እንደሚያስከትል ጥናቱ አረጋግጧል፡፡

በመካከለኛ እና ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ባላቸው ሀገሮች ከማጨስ ጋር በተያያዘ 80 በመቶ በላይ ሰዎች እንደሚሞቱ የተገለፀ ሲሆን፣ የአጫሾች ቁጥር በጨመረ መጠን የሟቾች ቁጥር እንደሚጨምርም ጥናቱ አክሏል፡፡

የአለም ጤና ድርጅት  እንደገለፀው  አብዛኛዎቹ  ሀገራት   ጤናማ ኑሮ ለማስፈንና   የሲጋራ አጠቃቀምን ለመቀነስ  በስጋራ ገበያዎች ላይ  ክልከላ፣  በሲጋራ እሽጎች   ላይ ማስጠንቀቂያ  እና የዋጋ ጭማሪ  ቢያደርጉም ለወጡ ግን  እምብዛም ነው፡፡

በ2013/14  በአለም ላይ  ከሲጋራ ቀረጥ የተገኘው  ገቢ  269 ቢሊዮን ዶላር  ሲሆን  በሲጋራ  ምክንያት ከተፈጠረውን  የአለም ኢኮኖሚ ክስረት  ጋር ሲስተያይ  ኪሳው የገዘፈ በመሆኑ ችግሩ የሚያደርሰውን ጉዳት ለመከላከል መንግስታት ተጨባጭ እርምጃ እንዲወስዱ   ድርጅቱ  አሳስቧል፡፡

የጤና ባለሙያዎች  የትምባሆ አጠቃቀም ሊከላከሉት የሚችሉ ነገር ግን  በአለም ላይ  ለብዙዎች  የሞት መንስኤ የሆነ ነው ብለዋል ፡፡

ምንጭ ፡ሮይተርስ

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy