Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ሶስት የኢንዱስትሪ ፓርኮች በ10 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ሊገነቡ ነው

0 339

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ሶስት የኢንዱስትሪ ፓርኮች በ10 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ሊገነቡ ነው

ሶስት የኢንዱስትሪ ፓርኮች በ10 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ሊገነቡ ነው

10 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ወጪ የሚደረግባቸው ሶስት የኢንዱስትሪ ፓርኮች በቀጣይ 12 ወራት ውስጥ ሊገነቡ ነው።

በቂሊንጦ፣ በቦሌ ለሚ ምዕራፍ 2 እና በጅማ የሚገነቡት ፓርኮች መድሃኒት እና የህክምና እቃዎች እንዲሁም ጨርቃ ጨርቅና አልባሳት የሚመረቱባቸው ናቸው።

የቂሊንጦና የቦሌ ለሚ ምእራፍ ሁለት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ከአለም ባንክ በተገኘ ብድር ይገነባሉ። የጅማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ደግሞ ሙሉ ወጪው በመንግስት ይሸፈናል።

በዛሬው እለትም የኢንዱስትሪ ፓርኮቹን ለመገንባት የሚያስችል ስምምነት ተፈርሟል።

279 ሄክታር መሬት ላይ የሚያርፈው የቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ 5 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ወጪ ይደረግበታል፤ በፓርኩ መድሃኒት እና የህክምና እቃዎች የሚመረቱ ይሆናል።

የቦሌ ለሚ ምዕራፍ 2 የኢንዱስትሪ ፓርክ ደግሞ 170 ሄክታር መሬት ላይ የሚገነባ ሲሆን፥ 3 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ወጪ ይደረግበታል።

75 ሄክታር መሬት ላይ የሚገነባው የጂማ ኢንዱስትሪ ፓርክም 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ይወጣበታል።

በቦሌ ለሚ ምዕራፍ 2 እና በጂማ ኢንዱስትሪ ፓርኮች አልባሳት እና ጨርቃ ጨርቅ ይመረታሉ።

በግንባታ ምክንያት ለሚነሱ ዜጎችም ምትክ መሬት የሚሰጣቸው ሲሆን፥ በፓርኮቹ የግንባታ ሂደት እና ከተጠናቀቁም በኋላ ቋሚ የስራ እድል እንዲፈጠርላቸው ይደረጋል ተብሏል።

የፓርኮቹ አካል 20 በመቶ በአረንጓዴ ተክሎች እንዲሸፈኑ መታቀዱም ነው የተገለጸው።

የቂሊንጦ እና ቦሌ ለሚ ምዕራፍ 2 የኢንዱስትሪ ፓርኮች ግንባታ በ12 ወራት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል።

የጂማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ደግሞ በዘጠኝ ወራት ውስጥ ተጠናቆ አምራቾች እንደሚገቡበት ተገልጿል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy