መድሃኒት በሚላመዱ ባክቴሪያዎች ላይ የሚያደርጉት ጥናት ውጤታማ ደረጃ ላይ መድረሱን ተመራማሪዎች አስታወቁ፡፡
ተመራማሪዎቹ ይፋ እንዳደረጉት መድሃኒት የሚለማመዱ ባክቴሪያዎችን የመቋቋም ሃይል ያላቸውን ሞለኪዮሎች በማበልፀግ በባክቴሪያ የሚተላለፉ በሽታዎችን ለመቋቋም የሚያስችል በር ከፋች ደረጃ ላይ መድረሳቸውን ተናግረዋል፡፡
ተመራማሪቹ ያበለፀጉት ግኝት ፀረ ባክቴሪያ መድሃኒቶችን የተለማመዱ ባክቴሪያዎችን በመቋቋም የተሸለ ውጤት የሚያመጡ መድሃኒቶችን ለመስራት በር የሚከፍት መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የተባበሩት መንግስታት በ2014 ባወጣው ትምበያ መሰረት እ ኤ አ በ2050 መድሃኒት በሚለማዱ ባክቴሪያ በሚመጡ በሽታዎች ሳቢያ 300 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች ሊሞቱ እንደሚችሉና ይህም ከፍተኛ ስጋት የሚፈጥር ጉዳይ መሆኑን የተባባሩት መንግስታት ድርጅት ገልጿል፡፡
በተላላፊ ባክቴሪያ የሚከሰቱ እንደ ሳምባ ምች( pneumonia) የአንጀት ኢንፌክሽን( E. coli) እና እንደ አባለዘር በሽታዎች ያሉ በቀላሉ በቁጥጥር ስር ሊዉሉ የሚችሉ በሽታዎች በአሁኑ ሰአት በፍጥነት እየተስፋፉና ፀረ ባክቴሪያ መድሃኒቶችን እየተለማዱ መሆኑን ተመራማሪዎቹ ገልጸዋል፡፡
በቀጣይም አዳዲስ መድሃኒቶችን ይዘው ለመቅረብ በፍጥነት መንቀሳቀስ እንደሚያስፈልግና የአሁኑ ግኝታቸውም በር ከፋች መሆኑን ተመራማሪዎቹ አስታውቀዋል፡፡
ምንጭ ፡ሳይቲስት አለርት