NEWS

በቅማንት ህዝብ የሚነሳው የማንነት ጥያቄ

By Admin

January 25, 2017

በቅማንት ህዝብ  የሚነሳው የማንነት ጥያቄ በዘላቂነት ለመፍታት ህገ መንግስቱን መሰረት ባደረገ መልኩ ህብረተሰቡን ሙሉ በሙሉ በማሳተፍ ህዝበ ውሳኔ እንደሚከናወን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ተናገሩ፡፡

የቅማንት የራስ አስተዳደር ጥያቄን በህብረተሰቡ ተሳትፎ ምላሽ ለመስጠት ያለመ የሰላም ኮንፈረንስ በጎንደር ከተማ ተካሂዷል፡፡

የቅማንትንና የአማራውን የሁለትዮሽና የህታማመችነት የሚያጠናክር ህዝባዊ ኮንፈረንስ በጎንደር ከተማ ተካሂዷል፡፡በኮንፈረንሱእንደተገለጸውም የቅማንትን ማህበረሰብ ራስን በራስ የማስተዳደር መብት በህገ-መንግስቱ መሰረት መመለሱ ይታወሳል፡፡ነገርግን የቀበሌዎችን ወሰን እስካሁን ባለመወሰኑ መላ ህዝቡን ያሳተፈ ህዝበ ውሳኔ እንደሚካሄድ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደርአቶ ገዱ አንዳርጋቸው ገልጠዋል፡፡ርዕሰ መስተዳደርሩ እንዳሉትም  ህዝበ ውሳኔው የድንበር ኩታ ገጠም ቦታዎችን በአግባቡበመለየት ይከናወናል፡፡

በኮንፈረንሱየተገኙት የሁለቱም ህዝቦች ተወካዮች ህገ-መንግስቱ በሚፈቅደው መ፤ሉ በአግባቡ ሊከናወን ይገባል፡፡ችግሩም ያለ ከታችኛውየቀበሌ አመራሮች በመሆኑ የክልልና የዞን አመራሮች ወርዳችሁ ልታዩ ይገባልም ብለዋል፡፡

በኮንፈረንሱ ከክልል እሰከ ዞን አመራሮችና የሁለቱም ህዝቦች ተወካዮች በተገኙበት በጎንደር ከተማ ተካሂዷል፡፡

አብዮት ይግዛው