Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በአማራ ክልል በ997 አመራሮች ላይ እርምጃ ተወሰደ

0 446

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

Fበአማራ ክልል በ997 አመራሮች ላይ እርምጃ ተወሰደ

በአማራ ክልል በ997 አመራሮች ላይ እርምጃ ተወሰደ

ባህር ዳር ታህሳስ 26/2009 በአማራ ክልል በጥልቅ ተሃድሶ ግምገማ መሠረት በ997 አመራሮች ላይ እርምጃ መወሰዱን የክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

የጽህፈት ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ንጉሱ ጥላሁን ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ በጥልቅ ተሃድሶ ግምገማው ከክልል እስከ ወረዳ የሚገኙ አመራሮች ተገምግመው ተለይተዋል።

በተደረገው የማጥራት ግምገማም 249ኙ አመራሮች በማስጠንቀቂያ የታለፉ ሲሆን 748ቱ ደግሞ ከነበሩበት የኃላፊነት ቦታ ተነስተው ዝቅ ብለው እንዲመደቡ ተደርጓል።

በሙስና በኪራይ ሰብሳቢነት ተግባርና በብልሹ አሰራር ተሳትፈዋል በሚል ከህብረተሰቡ ጥቆማ የቀረበባቸው ሌሎች 240 አመራሮች ደግሞ በየደረጃው በተቋቋሙ አጣሪ ኮሚቴዎች ጉዳያቸው እየተጣራ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡

ጉዳያቸው በመጣራት ላይ ከሚገኙ መካከል 15ቱ ከፍተኛ አመራሮች ናቸው፡፡

”በአጣሪ ኮሚቴው ጉዳያቸው ተጣርቶ ጥፋተኛ ሆነው የተገኙትን አመራሮች ወደ ህግ በማቅረብ በአጠፉት ልክ እንዲጠየቁ ይደረጋል” ብለዋል።

በተደረገው መልሶ የማደረጃት ስራም ከ700 በላይ አመራሮችን በአዲስ ወደ አመራርነት ማምጣት እንደተቻለ ተናግረዋል።

”ብቃትን፤ ውጤታማነትንና ተገቢነትን መሰረት አድርጎ በአዲስ የተዋቀረው አመራርም የክልሉን ልማት ለማፋጠን ጠንክሮ መስራት አለበት” ብለዋል።

በ15 ዓመታት የተሃድሶ ግምገማው ሂደት አባላቱና መላ ህብረተሰቡን ባሳተፈ መልኩ መካሄዱ የአመራሩን ጥንካሬና ድክመት ለይቶ በማንሳት እንዲታገል ጉልህ ድርሻ አበርክቷል ብለዋል።

በግምገማ ሂደቱም የአስተሳሰብ ግልፅነትና የገጠሙ ችግሮች በልካቸው ለመረዳት ያስቻለ ከመሆኑም በላይ የችግሮች መነሻ ምን እንደሆነም የጋራ መግባባት እንዲፈጠር ማስቻሉን ተናግረዋል፡፡

በክልሉ ዘላቂና አስተማማኝ ሰላም በማስፈን ድህነትን ለመቅረፍ መንግስትና ህዝብ እጅና ጓንት ሆነው እንደሚሰሩም  አስታውቀዋል፡፡

”በቀጣይ ስድስት ወራት የህዝቡን አንገብጋቢ ችግሮች ለይቶ ለመፍታትና የተፈጥሮ ሃብት፤ የትምህርት፤ የጤናና ሌሎች የልማት ስራዎች ትኩረት ተሰጥቶ እንዲሰራም አቅጣጫ ተቀምጧል” ብለዋል።

በጥልቀት የመታደስ ሂደቱም በቀጣይ ወደ ቀበሌ  እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።

በአማራ ክልል ህዝቡ የሚያነሳቸው ጥያቄዎች ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ባለፉት ወራት ከ7 ሺህ 100 በላይ አመራሮች በጥልቅ ተሃድሶ ግምገማ የማጥራት ስራ የተከናወነ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 5 ሺህ 595ቱ ባሉበት እንዲቀጥሉ መደረጉን አቶ ንጉሱ ጨምረው ገልፀዋል፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy