የአፍሪካ ሀገራት የኃይል አቅርቦት ችግርን ለመቅረፍ በአፍሪካ የታዳሽ ሃይል ኢንሺቲቭ በኩል የሚታቀዱ ኘሮጀክቶች ወደ ተግባር ሊገቡ እንደሚገባ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ገለፁ፡፡
በአፍሪካ የታዳሽ ሃይል ልማት ኢኒሺቲቭ የዳይሬክተሮች ቦርድ የመጀመሪያ ሰብሰባውን አካሂዷል፡፡
ኢትዮጵያ፣ ግብጽ፣ ቻድ፣ ናሚቢያና ጊኒ የቦርዱ አባል አገራት በሆኑበት መድረክ ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ያለ በቂ ኢነርጂ አፍሪካን ወደ ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ ማሸጋገር የማይታሰብ ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያ በኢኒሼቲቩ ዕቅድ በተካተቱት ጉዳዮች እንደምትስማማና ለተግባራዊነቱም በሙሉ አቅሟ እንደምትሰራ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም አረጋግጠዋል።
ኢኒሼቲቩን በዋናነት አፍሪካ ልማት ባንክ ፣ጀርመንና ፈረንሳይም ድጋፍ ያደርጉለታል።