NEWS

በኦጋዴን ተፋሰስ እስከ አራት ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር የሚደርስ የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት ተገኘ።

By Admin

January 11, 2017

በኦጋዴን ተፋሰስ እስከ አራት ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር የሚደርስ የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት ተገኘ። በኢትዮጵያ የተፈጥሮ ጋዝ ፍልጋ ከተሰማሩት ኩባንያዎች መካከል ጂሲኤል የተባለው የቻይና ኩባንያ በኦጋዴን ተፋሰስ ካሉብና ሂላላ በተባሉት አካባቢዎች አምስት ጥልቅ ጉድጓድችን በመቆፈር በተገኘው መረጃ እስከ አራት ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር የሚደርስ የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት መገኘቱ አረጋግጧል። ኩባንያው ሂላል-7 የተባለው የነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ የጉድጓድ ቁፋሮ በትናንትናው እለት ጀምሯል። የነዳጅ ዘይትና የተፈጥሮ ጋዝ ጉድጓድ ቁፋሮ በስድስት ወራት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ የተገለፀ ሲሆን ከሶስት አመት በኃላ የተፈጥሮ ጋዝን ማውጣት እንደሚጀመርም ታውቋል።