Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በፕሬዚዳንት ትራምፕ የተላለፈውና ከሰባት ሃገራት የመጡ ስደተኞች እንዲወጡ የሚያዘው ትዕዛዝ ለጊዜው ታገደ

0 602

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የአሜሪካ የፌደራሉ ፍርድ ቤት በፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የተላለፈውንና ከሰባት ሃገራት የመጡ ስደተኞች እንዲወጡ የሚያዘውን ትዕዛዝ ለጊዜው አገደ።

የፕሬዚዳንቱን ትዕዛዝ ተከትሎ የአሜሪካ የሲቪል ነፃነት ህብረትን ጨምሮ ሌሎች ቡድኖች ለፌደራሉ ፍርድ ቤት አቤቱታቸውን አቅርበው ነበር።

ለዚህም ህጋዊ ሰነዶችን አቅርበው የፕሬዚዳንቱ ትዕዛዝ አግባብ አለመሆኑን አመልክተዋል።

የፌደራሉ ፍርድ ቤት ዳኞችም የትራምፕ አዲስ ትዕዛዝ ህጋዊነት የሌለው ነው በማለት ለጊዜው አግደውታል።

በትራምፕ ከአሜሪካ እንዲወጡ ትዕዛዝ የተሰጠባቸው፥ የኢራን፣ ሊቢያ፣ ሶማሊያ፣ ሶሪያ፣ የመን፣ ኢራቅና ሱዳን ዜጎች ናቸው።

ትዕዛዙ አሸባሪዎች ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ ለማስቆም በሚል በዶናልድ ትራምፕ ለ90 ቀናት የተላለፈ ነበር።

ከአሜሪካ እንዲወጡ ውሳኔ የተላለፈባቸው ሰዎች ብዛትም እስከ 200 ይደርሳል ተብሏል።

ሰዎቹ ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸው እና ተዘዋውረው የመስራት ሙሉ ፈቃድም ያላቸው ናቸው።

የፕሬዚዳንቱን ትዕዛዝ ተከትሎም ዳላስና ኒውዮርክ በመሳሰሉት አውሮፕላን ማረፊያዎች ተከማችተው ነበር።

ከዛሬው የፍርድ ቤቱ ውሳኔ በኋላ ግን በነበሩበት እንዲቆዩ ይደረጋል፤ ጠበቃም ይቆምላቸዋል ነው የተባለው።

ስደተኞችን በአሜሪካ ተቀብሎ ማስተናገድ ለ120 ቀናት የታገደ ሲሆን፥ በ2017 ለስደተኞች የሚሰጠው ፈቃድ መጠንም ዝቅ እንዲል ተደርጓል።

ምንጭ፦ አልጀዚራ

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy