DEVELOPMENT

ባለስልጣኑ 312 ሰራተኞችን ከስራ ማሰናበቱን አስታወቀ

By Admin

January 28, 2017

ባለፉት ሁለት አመታት ብልሹ አሰራርን በመከተል ግብር ከፋዩን ለእንግልትና አላስፈላጊ ወጪ የዳረጉ 312 ሰራተኞችን ከስራ ማሰናበቱን የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን አስታወቀ።

ባለስልጣኑ ከመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ጋር በግብር አከፋፈልና ተያያዠ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርጓል።

በዚህም ከሰራተኞች ጋር ተያይዞ የሚያገጥሙ ችግሮችን ለመፍታት በተሰራ ስራ በብልሹ አሰራር ውስጥ የተዘፈቁ ሰራተኞች ከስራ እንዲባረሩ መደረጉን ገልጿል።

የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አብርሃም ንጉሴ ግብር ከፋዩ የ31 በመቶ እድገት ቢያሳይም ኢኮኖሚው ባመነጨው ልክ ግን የገቢ ግብሩ እየተሰበሰብ አይደለም ብለዋል።

ኮንትሮባንድ፣ ታክስ ማጭበርበር እና ኪራይ ሰብሳቢነት ደግሞ የችግሩ መንስኤ መሆናቸውን ነው ያብራሩት።

ይህን መሰረት ያደረገ የቁጥጥር ስራ እየተሰራ ነው ያሉት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ፥ የሚወሰደው እርምጃ ውጤቱ በተጨባጭ እስኪመጣ ድረስ ከሌሎች ስራዎች ጎን ለጎን ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። FBC