Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

አፍሪካን ከሰሜን እስከ ደቡብ የሚያገናኝ ወጥ የኤሌክትሪክ መስመር ሊዘረጋ ነው

0 517

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

አፍሪካን ከሰሜን እስከ ደቡብ የሚያገናኝ ወጥ የኤሌክትሪክ መስመር ሊዘረጋ ነው።

እቅዱ ይፋ የሆነው በታንዛኒያ እየተካሄደ  ባለው 24ኛው የምስራቅ አፍሪካ የኃይል ፑል ንዑስ ኮሚቴ  ስብሰባ ላይ ነው።

የታንዛኒያው የኢነርጂና  ማእድን ሚኒስትር  ፕሮፌሰር ሶስፔተር ሙሁንጎ እንዳሉት

የሰሜንና ደቡብ  የአፍሪካ ሀገሮችን  ከግብፅ ካይሮ እስከ   ደብቡብ አፍሪካ  ኬፕ ታዎን  በዘላቂ የኤሌትሪክ መስመር ለማገናኘት  የሚደረገው ጥረት በሶስት አመት ውስጥ ሊጠናቀቅ  ይችላል ብለዋል።

በመጪው ሚያዚያ የሚካሄደው ልዩ  ስብስባም ለዚህ ታልቅ አህጉራዊ  ፕሮጀክት ምቹ  ሁኔታዎችን በመፈተሽ ፕሮጀክቱ እውን በሚሆንበት መንገድ ላይ ይመክራል ብለዋል።

ከዚሁ ስብስባ  ጎንለጎን የተካሄደው የምስራቅ አፍሪካ የኃይል ፑል የሚንስትሮች ምክር ቤት ልዩ  ጉባኤም አገርን ከአገር  በሚያስትሳስረው የኃይል ፕሮጀክት ላይ መክሯል።

የምስራቅ አፍሪካ የኃይል ፑል ዋና  ፀሃፊ ሌቢ ቻንጉላህ እንዳሉት የቀጠናው የኃይል ፑል በርካታ  አገራትን በተለይም ኢትዮጵያን  ከኬኒያ፣ከጅቡቲ፣ከታንዛኒያና ዛምቢያ እንዲሁም ከሱዳንና ከግብፅ ጋር በማስተሳስር ላይ ይገኛል ብለዋል።በመሆኑም የምስራቅ አፍሪካ  የኃይል ትስስር  ለአህጉራዊ ትስስሩ  ቁልፉን ሚና  እንደሚወጣ ተናግረዋል።

መቀመጫውን በአዲስ አበባ  በማድረግ እኤአ በ2005 የተመሰረተው የምስራቅ አፍሪካ የኃይል ፑል ኢትዮጵያን፣ዲሞክራትክ ኮንጎን፣ ብሩንዲን፣ሩዋንዳ፣ኬንያ፣ታንዛኒያ ፣ሱዳን፣ ግብፅና ሊቢያን ያቀፈ ሲሆን ደቡብ ሱዳንና  ጁቡቲ  ደግሞ በቅርቡ ይቀላቀላሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ምንጭ ፥ ዴይሊኒውስ ታንዛኒያ

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy