ኢትዮጵያና አልጀሪያ በአህጉራዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት ተሰማሙ
ታህሳስ 30፣2009
ኢትዮጵያና አልጀሪያ በአህጉራዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት ተሰማሙ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳአለኝ በጋና አክራ ከአልጀርያ ብሔራዊ ምክር ቤት ኘሬዝዳንት አብዱልቃድር ቤነ ሳለህ ጋር ተወያይተዋል፡፡
ሁለቱ ሀገራት በቅርቡ የሚካሄደው የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ምርጫ በተሳካ ሁኔታ እንዲካሄድና ተመራጩ ሰው የህብረቱን ዓላማዎች ለማሳካት ያሳካ ዘንድ ድጋፍ ማድረግ በሚቻልበት ጉዳይ ላይም በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል፡፡
የአህጉሪቱን ዕድገት ወደ ኋላ እየጎተቱ ያሉ ግጭቶችን በማስቆም ለዘላቂ ዕድገትና ልማት በጋራ እንደሚሰሩም ነው የገለፁት፡፡
በሁለትዮሽ ጉዳይ ላይ የተደረሱ ስምምነቶችን ለመተግበር እንዲቻል የጋራ ኮሚሽን ሰብሰባ ለማድረግ ከመግባባት ላይ ደርሰዋል፡፡
ሪፖርተር:- ብሩክ ያሬድ