CURRENT

ኢትዮጵያ በድርቅ አደጋ የሚከሰት ጉዳትን ለመቀነስ የምታደርገው ጥረት እንደሚደግፍ ተ.መ.ድ አስታወቀ

By Admin

January 30, 2017

ኢትዮጵያ በድርቅ አደጋ የሚከሰት ጉዳትን ለመቀነስ የምታደርገው ጥረት ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ።

በአፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ለመታደም አዲስ አበባ የገቡት የተባበሩት መንግስታት ረዳት ዋና ጸሐፊና የአፍሪካ የአደጋ መከላከያ ተቋም ዋና ዳይሬክተር መሀመድ ኤቡጄ ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ የሚከሰቱ የድርቅ አደጋዎች የሚያደርሱትን ጉዳት ለመቀነስና ለመቆጣጠር እያክለናወነች ያለው ተግባር የሚደነቅ መሆኑን ተናግረዋል።

ረዳትዋና አሐፊው የኢትዮጵያ መንግስት በድርቅ አደጋ የሚከሰት ጉዳትን ለመቀነስ የሚያደርገው ጥረት ለመደገፍ ተቋማቸው ቁርጠኛ መሆኑን ተናግረዋል።

የአፍሪካ አገራት በድርቅ ምክንያት የሚከሰቱ አደጋዎችና የሚያደርሱት ጉዳት ለመቀነስ የቅድመ አደጋ መከላከል ስርአት በመዘርጋት ፈጣን ምላሽ የሚሰጥ የአሰራ ዘዴ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባቸውም አሳስበዋል።

ሪፖርተር:- ሳሙኤል ዮሀንስ