ኢትዮጵያ የመጀመርያውን የፀጥታ ምክር ቤት ጉባኤ ላይ ተሳተፈች። የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በተገኙበት የተካሄደው የመጀመሪያውን የፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ተሳትፈዋል። አዲሱ የተመድ ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝም በዋና ፀሃፊነት ለመጀመሪያ ጊዜ በመሩት ስብሰባ ላይ በዓለም ሰላም ማስጠበቅ እና ግጭት መከላከል ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል። የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ በስብሰባው ላይ ባደረጉት ንግግር የቀድሞ ዋና ፀሃፊ ባን ኪሙን የፓሪሱ የዓየር ንብረት ለውጥ ስምምነት እንዲፈረም እና የ2030 የልማት አጀንዳ ተዘጋጅቶ እንዲፀድቅ ያበረከቱት አስተዋፅኦን በማውሳት ላበረከቱት አስተዋፅኦ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ግጭትን ለመከላከል እና ለማስቆም እየሰራች ያለችው ስራ አጠናክራ እንደምትቀጥልሞ ዶክተር ወርቅነህ አረጋግጠዋል።