Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ከኢህአዴግ ምክር ቤት ፅህፈት ቤት የተሰጠ መግለጫ

0 357

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ከኢህአዴግ ምክር ቤት ፅህፈት ቤት የተሰጠ መግለጫ

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ከታህሳስ 22-23/2009 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በጥልቀት የመታደስ ንቅናቄ መድረኮች በተቀመጠላቸው አቅጣጫ መሰረት እየቀጠሉ እንደሆነ ገምግሟል፡፡

ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው እንደገና በጥልቀት የመታደስ የንቅናቄ መድረኮች በተቀመጠላቸው አቅጣጫ መሰረት በየደረጃው በተካሄዱ የግምገማ መድረኮች ከከፍተኛ አመራሩ ጀምሮ እስከ አባሉ ድረስ የተሳተፉበትና በአጀንዳዎቹ ላይም የጋራ መግባባት የተደረሰባቸው እንደነበሩ ተመልክቷል፡፡

የኪራይ ሰብሳቢነት አስተሳሰብና ተግባር ወኪል የሆኑት ትምክህት፣ ጠባብነትና የሃይማኖት አክራሪነት እንዲሁም ስልጣንን ለግል ጥቅም የማዋል አመለካከትና ተግባር ድርጅቱንና ልማታዊ ዴሞክራሲያዊ ስርዓቱን በመስቀለኛ መንገድ ላይ እንዲሆኑ ያደረጉ የህዳሴያችን አደጋዎች መሆናቸው እንዲጋለጥ በየደረጃው ብቁ ትግል የተካሄደባቸው መሆኑን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ተግባብቶበታል፡፡

በየደረጃው ባለ አመራርና አባላት በአስተሳሰብ ደረጃ የትምክህትና ጠባብነት አመለካከትና ተግባራት የፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ስርዓቱን የሚፈታተኑ ጠንቆችና ሀገሪቱንና ህዝቦቿን ለቀውስ የሚዳርጉ የጥፋት አመለካከቶች መሆናቸው ላይም የጋራ አቋም ተይዞባቸዋል፡፡ እነዚህን ችግሮችም ታግለን በፍጥነት በማረም አዳጊ ፍላጎት ያለው ሕብረተሰባችንን የማርካትና የተጀመረውን የህዳሴ ጎዞ የማስቀጠል ጉዳይ ትልቅ ትርጉም ያለው መሆኑ አፅንኦት ሰጥቶበታል፡፡

በጥልቀት የመታደስ መድረኩ ከላይ እስከ ታች ሁሉም አመራሮች፣ አባላት ያላንዳች መሸማቀቅ የተሰማቸውን ሐሳብ በሙሉ በግልፅ በማቅረብ የድርጅቱን የውስጠ ዴሞክራሲ ችግሮች በሚያርምና በሂደቱም ዴሞክራሲያዊ አንድነትን በሚያጎለብት አኳኋን መፈፀሙን አረጋግጣል፡፡ በዚህ ሂደት የፀረ-ዴሞክራሲ፣ አደርባይነት፣ በትስስር የመስራት አሰራሮችን በማረም በአባላትና በአመራር መካከል ጓዳዊ ትስስርን በማጠማከር መተማመንን በሚያጎለብት ሁኔታ መፈፀሙን ተመልክቷል፡፡

በድርጅቱ ውስጥ በተደረጉ ትግሎች ሙስናና ብልሹ አሰራሮች በየትኛውም ደረጃና መልኩ የሚገለፁ ያለምንም ምህረት ፖለቲካዊ ትግል በማደረግ የተጋለጡ ሲሆን ከዚህ በመነሳትም ፖለቲካዊ፣ አስተዳደራዊ እና ሕጋዊ እርምጃዎች የተወሰዱ መሆኑ የገመገመው ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው በግምገማ መድረኮች የማይጋለጡ ከሙስና ውስበስብ ባህርይ ጋር የተያያዙ ጉዳችን በሚመለከት በሁሉም ደረጃዎች ጥናቶችና ፍተሻዎች ተጠናክሮው እንዲቀጥሉ ወስኗል፡፡

በጥልቀት የመታደስ ሂደቱ በየደረጃው ውይይት የተካሄደበትና መግባባት ተደረሰበት ሌላው ጉዳይ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ስርዓቱ ከአደረጃጀቱ ጀምሮ የእኩል ተሳታፊነትና ፍትሓዊ ተጠቃሚነትን በሚያረጋግጥ መንገድ የተደራጀ መሆኑና ይህንኑ አድሎ ያለ በማስመሰል ይካሄድ የነበረው አፍራሽ እንቅስቃሴ ስህተት መሆኑ የተጋለጠ ሲሆን ሁሉም የሀገራች ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በየአካባቢያቸው ያሏቸውን ፀጋ እያለሙና እየተጠቀሙ በሀገራዊ ጉዳይ እኩል ተሳታፊና ፍትሐዊ ተጠቃሚ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ስራ ማሳለጥ እንደሚገባ አስመሮበታል፡፡

ከግምገማዎቹ በማስቀጠልም የአመራር ሽግሽግና የመንግስትን መልሶ ማደራጀት ስራዎች በተቀመጠላቸው አቅጣጫ መሰረት እየተፈፀሙ መሆኑን አረጋግጧል፡፡ የመልሶ ማደራጀት ስራው ከዚህ በፊት የድርጅትና የመንግስት ስልጣን ስምሪት አንድና ያው አድርጎ የማየት ሁኔታ በሚያርም መልኩ እየተከናወነ መሆኑን ተመልክቷል፡፡ ምደባው የድርጅትና የመንግስት ስራን በሚለይ መንገድ መንግስት መልሶ በሚደራጅበት ወቅት ከድርጅቱ አባላትና አመራሮች በተጨማሪ አባላት ባይሆኑም በሕገ-መንግስቱና በፖሊሲዎቻችን ላይ የተሟላ ግልፅነት ያላቸው፣ ከዚህ በፊት በነበራቸው ስምሪት ውጤታማ የሆኑ፣ ህዝብንና ሀገርን ለማገልገል ቁርጠኛ የሆኑ ምሁራን ባካተተ መልኩ መፈፀሙ በዝርዝር ተመልክቷል፡፡

የአመራር ምደባው በሚካሄድበት ወቅት አዲስ ተመዳቢዎች ለህዝብ አስተያየት የማቅረብ ስራው በዞኖችና በከተሞች እየተፈፀመ ያለው ሂደት ትልቅ ልምድ የተገኘበት በመሆኑ በቀጣይም ተጠናክሮ የሚቀጥልና ህዝቡ በመንግስት የአመራር ስምሪት ስርዓት ላይ ባለቤትነቱን እንዲያረጋግጥ እንደሚያስችልም ገምግሟል፡፡

ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው በየደረጃው ህዝቡ ሲነሳቸው የነበሩ ፈጣን ምላሽ የሚሹ ጉዳዮች አፋጣኝ መፍትሔ እንደሚሰጣቸው የደመደመ ሲሆን በተለይ የወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ፣ የአገልግሎት አሰጣጥ፣ ከፍትሕ አካላት ጋር ተያይዘው የሚስተዋሉ ችግሮች እንዲሁም ከወሰን ማካለል ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ለመፍታት ምቹ ሁኔታ ከመፍጠሩም በላይ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷቸው መፈታት እንዳለባቸው አፅንኦት ሰጥቶበታል፡፡

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በአገሪቱ ተጋርጦ ነበረውን የጥፋት ውጥን በማክሸፍ ትልቅ አስተዋፅኦ አበርክቷል ያለው ኮሚቴው የተጀመረው ሀገራዊ የጥልቅ ተሃድሶ ንቅናቄ ለማሳካት ምቹ ሁኔታ መፈጠሩንም አስምሮበታል፡፡ አዋጁ የፀረ-ሰላም ኃይሎች ሀገርን የማፍረስ ተልእኮ በማክሸፍ በሀገራችን አንዣብቦ የነበረውን የዜጎች ሰላምና ደህንነት ስጋት በአስተማማኝ ሁኔታ መቀልበስ ማስቻሉንም አውስቷል፡፡ መላው የሀገራችን ህዝቦች ሰላማቸው በመጠበቅም ሆነ አዋጁ በሚፈለገው ደረጃ እንዲተገበር ላደረጉት ያልተገደበ ተሳትፎ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ከፍተኛ አድናቆት እንዳለው ገልጿል፡፡

የሀገራችን ህዝቦች ኢህአዴግ በጀመረው እንደገና በጥልቀት የመታደስ ንቅናቄ ላይ ተስፋ እንዳላቸው የገመገመው ኮሚቴው ህዝቡ ያነሳቸው ጥያቄዎችና ቅሬታዎች እንዲፈቱለት በጉጉት እየጠበቀ እንደሆነም በየደረጃው ከተካሄዱት የተሃድሶ መድረኮች የጋራ መግባባት የተፈጠረበት ነው ብሏል፡፡ በቀጣይም የተጀመረው የተሃድሶ ንቅናቄ ግለቱን ጠብቆ እንዲሄድ ለማድረግ ወደ ተግባር የሚያስገቡ የንቅናቄ መድረኮችን ከወጣቶች፣ ከመንግስት ስራተኞችና ህዝቡ ጋር ለማካሄድ የሚያስችሉ ዝግጅቶች የተጠናቀቁ በመሆኑ በጥራት መከናወን እንዳለባቸው ውሳኔ አሳልፏል፡፡

ዴሞክራሲያዊ የመድብለ ፓርቲ ስርዓቱ ይበልጥ እንዲጎለብት ከማድረግ አኳያ ኢህአዴግ ትናንትም ሆነ ዛሬ ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ በፅናት እንደሚታገል የገለፀው ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ከወሰኑት ማናቸውም የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ውይይት፣ ክርክርና ድርድር ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ይፋ አድርጓል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ ኢህአዴግ ከሲቪክ ማሕበራት እና ምሁራን እንዲሁም የሃገራችን ሰላም፣ ልማትና ዴሞክራሲ በማጎልበት ረገድ ሚና ካላቸው ሌሎች ወገኖች ሁሉ በአጋርነት ለመስራት በድጋሚ ዝግጁ መሆኑን ገልጿል፡፡

በባለፉት ተከታታይ ዓመታት የተመዘገበው ፈጣንና ተከታታይ ኢኮኖሚያዊ እድገት በያዝነው ዓመታም ቀጥሏል ያለው የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሽን ዕቅድ በተሟላ ሁኔታ ተግባራዊ ለማድረግም መላው የሀገራችን ህዝቦችና ሁሉም አካላት ርብርብ እንዲያደርጉ ጥሪውን አቅርቧል፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy