ኮማንድ ፖስቱ ከህዝብ ጋር ተቀናጅቶ በመስራቱ ተጨባጭ ውጤት መምጣቱን ገለፀ
ከሁሉም ክልሎች የተውጣጡ የፀጥታ አካላት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት እቅድ አፈፃፀምን ገምግሟል።
በኮማንድ ፖስቱ ታቅደው ሲስሩ የነበሩ ተግባራት ከሶስት ወራት በኋላ ምን ያህል ውጤታማ እንደሆኑ ከፌደራልና ከክልል የተውጣጡት የፀጥታ አካላት ገምግመውታል።
በዚህም ህዝብን ባሳተፈ መልኩ የተሰራው ስራ ተጨባጭ ውጤት ማምጣቱን ነው የኮማንድ ፖስቱ ሴክሬታሪያት አቶ ሲራጅ ፈጌሳ ለኢቢሲ የገለፁት።
በመድረኩ ለውጦች ቢኖሩም አሁንም አልፎ አልፎ የሚታዩ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት የተቀናጀ ስራ መስራት እንደሚገባ መወሰኑንም አቶ ሲራጅ ተናግረዋል።
ኮማንድ ፖስቱ በቀጣይ በሚያከናውናቸው ተግባራት ላይ በመምከር አቅጣጫ እንደሚያስቀምጥም ተገልጿል።