Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ውይይት እንጂ ማግለል መፍትሄ ይሆናል አትልም ኢትዮጵያ!

0 495

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ውይይት እንጂ ማግለል መፍትሄ ይሆናል አትልም – ኢትዮጵያ!

አባ መላኩ 01-09-17

ሰሞኑን አንዳንድ የግብጽ ሚዲያዎች ኢትዮጵያ ከመካከለኛው የምስራቅ አገሮች ጋር የምታደርጋቸውን የውጭ ግንኙነቶች በመልካም እየተመለከቷቸው አይደለም። የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ በአገሮች መካከል የጋራ ተጠቃሚነትን መሰረት ያደረገ በየትኛውም አገር የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባትን የሚከለክል ነው። ኢትዮጵያ በዚህ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲዋ ባለፉት 26 ዓመታት ውጤታማ መሆን ችላለች። ይሁንና የኢትዮጵያን የውጭ ግንኙነት መርህን በአግባብ ያልተገነዘቡ አሊያም የአገሪቱን ስም በቀና ማንሳት የማይፈልጉ አካላት ሁሉን ነገር በመጠራጠር መመልከትን ይመርጣሉ። በቅርቡ ኢትዮጵያ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች የተመራ ልዑክ በመካከለኛው ምስራቅ አገሮች የስራ ጉብኝት አድርጓል። በተመሳሳይ የእነዚህ አገሮች ልዑክም በኢትዮጵያ ጉብኝት ማድረግ የተለመደ ተግባር ነው። ይሁንና ይህን ግንኙነት አንዳንድ የግብጽ ሚዲያዎች ከታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ጋር ለማገናኘት ጥረት ሲያደርጉ ተስተውለዋል። ኢትዮጵያ የመካከለኛው ምስራቅን በተለይ ከሳዑዲ ዓረቢያ፣ ከካታርና ከተባበሩት የአረብ ኤሚሬትስ ጋር የምታደርገው ግንኙነት ግብጽን ከአረቡ አለም ለመነጠል አስባ ነው የሚል የተሳሳተ አስተሳሰብ ሲያራምዱ ታይተዋል። በመጀመሪያ ደረጃ የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ እንዲህ ያለ ነገርን ለማራመድ አይፈቅድም። ኢትዮጵያ የኢኮኖሚክ ዲፒሎማሲን መሰረት ያደረገው የውጭ ግንኙነት ፖሊሲዋ በአገሮች መካከል የጋራ ጥቅምን መሰረት ያደረገ፣ በህዝቦች መካከል የጋራ ተጠቃሚነትን መሰረት ያደረገ ነው። በመሆኑም ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያው በሳውዲ ዐረቢያ በነበራቸው ቆይታ ዋነኛ አላማ የህዝቦችን የጋራ ተጠቃሚነት የበለጠ ለማጎልበት የሚያስችሉ ኢኮኖሚያዊ እንጂ እንደአንዳንድ የግብጽ ሚዲያዎች እሳቤ አይደለም። አገሮች በጋራ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት በኢንቨስትመንትን፣ በወጪና ገቢ ምርቶች ሲተሰሰሩ ዘላቂ ዕድገትና አስተማማሽ ሰላም በአአገሮቹ መካከል ብቻ ሳይሆን በቀጠናውም ማምጣት ይችልሉ። ምክንያቱም ይህን አይነት አካሄድ በህዝቦች መካከል መተማመንና መደጋገፍን የሚፈጥረው በመሆኑ ነው። የናይል ተፋሰስ አገሮች የትብብር ማዕቀፍ ለማጽደቅ በሚደረግ ሂደት አንዳንድ የግብጽ ሚዲያዎች ኢትዮጵያ ግብጽን የሚያገል ስትራቴጂን እየተከተለች ነው የሚል ወቀሳ ሲሰነዝሩ ነበር። ይሁንና የትብብር ማዕቀፉ ለሁሉም የተፋሰሱ አገራት እኩል ክፍት ነበር። ግብጻዊያን በወቅቱ መድረኩን ያለመፈለግ አዝማሚያ በማሳየታቸው እንጂ ኢትዮጵያ ግብጽን ለማግለል አንዲት ጋት አልተራመደችም። በወቅቱ ኢትዮጵያ ይዛው የተነሳቸው ሃሳብ በሁሉም አገሮች ቅቡልነት ማግኘቱ እንጂ ኢትዮጵያ በማንም አገር ላይ ጫና አልፈጠረችም። በመርህ መከራከር የዲፕሎማሲ ብቃትን ያሳያል። የኢትዮጵያ መንግስት አቋም አሳታፊነት ነው። ምክንያቱም በማግለል አሊያም ነገሮችን በማደባበስ ዘላቂ መፍይሄ መስጠት አይቻልም። የኢትዮጵያ መንግስት እንኳን በእንዲህ ያለ ትላለቅ ጉዳይ ላይ ይቅርና በትናንሹ ጉዳዮችም ሁሉም የሚመለከተው አካል ተሳታፊ ካልሆነ የተፈለገው ውጤት ይመጣል ብሎ አያስብም። በናይል ተፋሰስ የትብብር 2 ማዕቀፍ ውይይት ወቅትም ግብጻዊያን አባይን ብቻዬን ልጠቀም የሚል የተሳሳተ አመለካከት ተነስተው ኢትዮጵያ በበጎ አልተመለከቷትም እንጂ ኢትዮጵያ ግብጽን ለመጉዳት አንዳችም እንቅስቃሴ አድርጋ አታውቅም። በወቅቱ አንዳንድ የግብጽ ሚዲያዎች ይሉት የነበረው ኢትዮጵያ የላይኞቹን የተፋሰስ አገራት አስተባበረች፣ የግብጽን ብሄራዊ ጥቅም የሚጎዳ ስምምነት ልታስፈርም ነው፣ የቀድሞዎቹን የናይል ስምምነቶች ተቀባይነት እንዳይኖራቸው ኢትዮጵያ ዘመቻ ከፍታለች ወዘተ በሚል የግል ጥቅምን ብቻ ታሳቢ ያደረገ ውንጀላ ሲያካሂዱ ነበር። ይሁንና የኢትዮጵያን በወቅቱ ስታራምደው የነበረው በተፋሰሱ አገራት መካከል ፍተሃዊ የውሃ ተጠቃሚነት መርህ መኖር አለበት፤ ይህ ካልሆነ የወንዙ ዘላቂ ጠቀሜታ(የተፋሰስ ልማት መጠናከር አለበት ) አደጋ ላይ ይወድቃል የሚል መከራከሪያ ኢትዮጵያ ይዛ በመቅረቧ በሁሉም የላይኞቹ የተፋሰስ አገራት ተቀባይነት አገኘ። ይህ የኢትዮጵያ አቋም አሁን ላይ በሁሉም የተፋሰሱ አገራት ግብጽን ጨምሮ ተቀባይነትን ማግኘት ችሏል። ሌባ እናት ልጇን አታምንም ይባላል። ግብጽ ስትመራው በቆየችው የናይል አገሮች ውይይቶች ላይ ከ86 በመቶው በላይ የናይልን ውሃ የምታመነጭን አገር (ኢትዮጵያ) ተገቢው ቦታ ተሰጥቷት አይውቅም ነበር። ግብጽ አንዲት ጠብታ ውሃ ለአባይ ሳታበረክት የውሃውን ሶስት አራተኛ ብቸኛ ባለመብት አድርጋ ትቆጥራለች። ማግለል ከተባለ ይህ ነው። ግብጻዊያን ከሱዳን ጋር ውሃ መከፋፈል ውስጥ ሲገቡ የኢትዮጵያን የውሃ ድርሻ መስጠት ይቅርና ክፍፍሉን አላሳወቋትም። በስምምነቱም ላይ እንድትገኝ አልተደረገችም። ማግለል ከተባለ ይህ ነው። ግብጽ በአንድ ወቅት በሌሎች ራስጌ አገሮች (ኢትዮጵያን ሳይጨምር) ይሁንታ ለማትረፍ ያላደረገችው ጥረት አልነበረም። ለአብነት ኡንዱጉ የተባለውን ማኀበር መመሥረት ነበር። ኡንዱጉ የስዋሕሊ ቃል ሲሆን፤ ትርጉሙም ወንድማማችነት፣ ጓደኝነት እንደ ማለት ነው። ግብፅ ይህንን ስትመሠርት መጠሪያው በስዋሕሊ እንዲሆን ያደረገችው አስባበት እንደሆነ መገንዘብ አያዳግትም። ይህ ማኀበር የተመሠረተው እ. ኤ. አ በ1983 ሲሆን የመጀመሪያውን ጉባኤ በካርቱም ከጥቅምት 2-4/1983፣ የሁለተኛውን በዛየር ኪንሻሳ ከመስከረም 3-4/1984፣ ሦስተኛውን በካይሮ ከነሐሴ 7-8/1985 ሌሎች ቀጣይ ስብሰባዎችም ከዚያ በኋላ ተካሂደዋል፡፡ እጅግ በጣም የሚያሳዝነውና የሚያስገርመው ነገር ቢኖር 86 በመቶ የዓባይ ምንጭ የሆነችው ኢትዮጵያ በማኀበሩ ውስጥ ያለመታቀፏ ነው። ግብፆች አንዳንዴ ሲያሰኛቸው ኢትዮጵያ በታዛቢነት እንድትገኝ አሊያም ደግሞ በተገቢው ሁኔታ ሃሳቧን እንዳታራምድ የተለያዩ ስልቶችን በመጠቀም ተገቢው ሚና እንዳይኖራት ሲያደርጉ ነበር። ኢትዮጵያ የራሷ የውስጥ ችግሮች መኖር እንደተጠበቁ ሆነው በዚህ ውይይት ላይ እስከ አምስተኛ ጉባኤ ድረስ አልፎ አልፎ ድምጿን ለማሰማት ከሞመከር ያለፈ እምብዛም የረባ እንቅስቃሴ ማደረግ አልቻለችም ነበር። ከዚያ ወዲህ ግን ናይል 2002 በተባለውና በኢትዮጵያ አቆጣጠር በ1993 ዓ. ም በተመሠረተው ጉባዔ ኢትዮጵያ በንቃት መሳተፍ ከመጀመሯም በላይ 5ኛውንና 8ኛውን በአገሯ የናይል ጉባዔ በማስተናገድ ወሳኝ የሆኑ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ ቻለች። የኢፌዴሪ መንግስት ከተቋቋመ ብኋላ ኢትዮጵያ አባይን በተመለከተ የምታራምደው አቋም የጸናና በየትኛውም መስፈርት ትክክልኛ የሚባል ነው። “ፍትሃዊ የውሃ ክፍፍል በሁሉም የተፋሰስ አገራት መካከል” የሚለው የኢትዮጵያ አቋም በሁሉም የተፋሰሱ አገራት ተቀባይነት ማግኘት ችሏል። ናይልን በተመለከተ ኢትዮጵያ የምታራምደው አቋም በደንብ የተተነተነና በደንብ ተየመከረበት ነው። የአካባቢውን ዘላቂ ሰላም የሚያረጋግጥ፣ 3 የውሃውን ዘላቂ ህይወት ታሳቢ ያደረገ ነው። “ዕኩል” እና “ፍትሃዊ” የሚባሉት ቃላት ለየቅል ናቸው። የኢፌዴሪ መንግስት ኢትዮጵያ የውሃውን ከ86 በመቶ በላይ አመንጪ በመሆኗ ትልቅ የውሃ ድርሻ ልውሰድ የሚል አቋም አልያዘም። እንደእኔ እንደኔ ይህ ነው ህዝባዊነት፤ ይህ ነው ለአካባቢው ዘላቂ ጥቅም ማሰብ፤ ይህ ነው አህጉራዊነት። አሁንም ኢትዮጵያ እንደቀድሞው ሁሉ ከመጋረጃው በስተጀርባ የምትሰራው አንድም ነገር የለም። የታላቁን የህዳሴ ግድብን በተመለከተ ኢትዮጵያ ሁሉም የተፋሰሱ አገራት የተሟላ መረጃ እንዲያገኙ አድርጋለች። ለአለም አቀፍ ጋዜጠኞች ሳይቀር መጎብኘት እንዲችሉ አድርጋለች። ለግብጻዊያንና ሱዳናዊያን በቂ መረጃ ሰኝታለች። ሱዳንዊያንኖች እውነታውን መርምረው ተረድተው ከኢትዮፕያ ጎን መቆም ችለዋል። ግብጻዊያን ወጣ ገባ የሚል አቋማቸው አሁንም አለቀቃቸውም። በኢትዮጵያ ፓርላማ ሽብርተኛ የተባሉ አካላትን በማስጠለል የሁከት ጥሪያቸውን በአደባባይ ሲያሰሙ ተስተውለዋል። የግብጽ መንግስት እጄ የለበትም ቢልም ነገሩን አያውቀውም ለማለት ግን አያስደፍርም። ይህ ድርጊት ኢትዮጵያ ፈጽማው ቢሆን ኖሮ ግብጻዊያን ነገሩን ምን ያህል ያጮሁት እንደነበር ሳስበው የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስትን የበሰለ አካሄድን አደንቃለሁ።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy