Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ተሳታፊዎች አዲስ አበባ መግባት ጀመሩ

0 749

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ተሳታፊዎች አዲስ አበባ መግባት ጀመሩ

በ28ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ከተለያዩ አገራት የሚመጡ እንግዶች አዲስ አበባ መግባት ጀመሩ።

መጀመራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው፥ በጉባኤው ከ32 በላይ የአፍሪካ አገራት መሪዎች ይሳተፋሉ።

ከጥር 14 እስከ 23 ቀን 2009 ዓ.ም የሚካሄደውን የህብረቱ የመሪዎች ጉባኤ በተሳካ ሁኔታ እንዲካሄድ ቅድመ ዝግጅቶች እየተጠናቀቁ መሆኑ ተገልጿል።

የሚኒስቴሩ ቃል-አቀባይ አቶ ተወልደ ሙሉጌታ እንዳሉት፥ በጉባኤው ለመሳተፍ 28 ፕሬዝዳንቶች፣ ሁለት ምክትል ፕሬዝዳንቶችና ሁለት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮች ከዛሬ ጀምሮ አዲስ አበባ መግባት ይጀምራሉ።

ከአፍሪካ ህብረት አባል አገራት ውጪ የሆኑ የ35 አገራት ከፍተኛ ባለስልጣናትና 25 የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ከፍተኛ ተወካዮችም የጉባኤው ተሳታፊ እንደሚሆኑ ይጠበቃል።

አገሪቷ የህብረቱ ዋና መቀመጫ ከመሆኗ ባለፈ ትልልቅ ጉባኤዎችን የማስተናገድ አቅሟ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየዳበረ መምጣቱንና 28ኛውን የህብረቱ የመሪዎች ጉባኤ በተሳካ ሁኔታ ለማስተናገድ ዝግጅቷን እያጠናቀቀች መሆኑንም አቶ ተወልደ ገልጸዋል።

ህዝቡ በተለይም የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ለዘመናት የዘለቀ የእንግዳ ተቀባይነት ባህሪውን በማስጠበቅ እንደተለመደው ጉባኤው ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ የተለመደ ትብብሩን እንዲያደርግም ጥሪ አቅርበዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy