Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የከተራና የጥምቀት በዓል በመላ ሀገሪቱ በሰላም መከበሩን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ገለፀ

0 1,710

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የከተራና የጥምቀት በዓል በመላ ሀገሪቱ በሰላም መከበሩን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ገለፀ

 

የከተራ እና የጥምቀት በዓል በመላ በመላ ሀገሪቱ ያለምንም የፀጥታ ችግር መከበሩን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

የኮሚሽኑ ፅህፈት ቤት ሃላፊ ረዳት ኮሚሽነር የማነ ገሰሰ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ የከተራ እና ጥምቀት በዓል በመላ ሀገሪቱ ያለምንም ችግር በሰላማዊ መንገድ በድምቀት ተከብረዋል።

በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ህብረሰተቡ በተለይም ወጣቱ ከፍተኛ ሚና መጫወቱን ያነሱት ረዳት ኮሚሽነሩ፥ የሃይማኖት አባቶች፣ ምእመናን እና የፀጥታ ሃይሎች በዓሉ በሰላም እንዲከበር ላደረጉት አስተዋፅኦ ምስጋና አቅርበዋል።

በቀጣይም ህብረተሰቡ ከፀጥታ ሀይሎች ጋር የሚያደርገውን ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥል ኮሚሽኑ ጥሪ አቅርቧል።

በበተመሳሳይ የከተራና የጥምቀት በዓል በሰላም መከበራቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

ኮሚሽኑ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ስፍራዎች የተከበሩት የከተራና የጥምቀት በዓላት ያለምንም የጸጥታ ችግር በሰላም ተጠናቀዋል።

የከተማው ነዋሪ በተለይ ወጣቱ ከጸጥታ ኃይሉ ጋር በመተባበር ለበአላቱ ድምቀትና በሰላም መከበር ከፍተኛ አስተዋፆ ማበርከታቸውን ኮሚሽኑ ገልጿል።

ከኪስ ውስጥ ሞባይል ስልክ እና ገንዘብ የሰረቁ አንዳንድ ግለሰቦች በህብረተሰቡና በፖሊስ አባላት እጅ ከፍንጅ ተይዘው ምርመራው እየተጣራባቸው እንደሆነ እና ከእነዚህ ደረቅ ወንጀሎች ውጪ በአላቱ ፍፁም ሰላማዊ በመሆነ ሁኔታ መከበራቸወን ኮሚሽኑ አስታውቋል።

ህብረተሰቡ ለከተማዋ ፀጥታ እውን መሆን እያደረገ ላለው ቀና ትብብር የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምስጋናውን ያቀረበ ሲሆን፥ ወደፊትም የከተማውን ጸጥታ ለማስከበር በሚሰሩ ልዩ ልዩ ተግባራት ነዋሪው ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል ኮሚሽኑ ጥሪውን አስተላልፏል።

ህብረተሰቡ በማንኛውም ወቅት ከፀጥታ ስራ ጋር ተያያዥ እና አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት ይሁን ጥቆማ ለመስጠት እንዲሁም የፖሊስ አገልግሎትን ለማግኘት 01-11-26-43-77፣ 01-11-26-43-59፣ 01-18-27-41-51፣ 01-11-11-01-11 እና በ991 ነፃ የስልክ መስመር መጠቀም እንደሚችል ኮሚሽኑ አስታውቋል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy