Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

28ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በአዲስአበባ በሕብረቱ አዳራሽ እየተካሄደ ነው።

0 643

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

28ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በአዲስአበባ በሕብረቱ አዳራሽ እየተካሄደ ነው።

በወጣቶች ላይ ኢንቨስት በማድረግ የህዝብን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ በሚል መሪ ቃል በሚከበረው የህብረቱ ጉባኤ የህብረቱ አባል ሃገራት መሪዎችንና የመንግስታቱን ድርጅት ዋና ጸሓፊ ጨምሮ በርካታ እንግዶች ተገኝተዋል።

በጉባኤው ንግግር ያደረጉት የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ዶክተር ንኮሳዛና ድላሚኒ ዞማ በአፍሪካ ለሴቶችና ለወጣቶች ለትምህርትና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ትኩረት መስጠት ያስፈልጋል ብለዋል ።

ሊቀመንበሯ የወጣቶች የስራ አጥንነትን ለመቅረፍ ሰፊ የስራ እድል በሚፈጥሩ ዘርፎች ማተኮር እንደሚገባም ተናግረዋል።

በጉባኤው ላይ ንግግር ያደረጉት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊው አንቶኒዮ ጉቴሬዝ የአፍሪካ ሕብረት በሰላምና ቀጠናዊ የኢኮኖሚ ትብብሮች እንዲጠናከሩ በሚያከናውኗቸው ስራዎች ላይ በጋራ እንሰራለን ብለዋል።

አንድ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ለመፍጠርና ነጻ አህጉራዊ የንግድ ትስስር እውን ለማድረግ አፍሪካ ለምታደርገው ትግል ስኬታማነት በጋራ እንደሚሰሩም ገልጸዋል።

ዋና ጸሓፊው አፍሪካ በዓለም ሰላም ማስከበር ተልእኮ ከፍተኛውን ድርሻ እየተወጣች መሆኗንም ተናግረዋል።

የፍልስጤሙ ፕሬዝዳንት ሙሀሙድ አባስ አፍሪካውያን ከፓን አፍሪካኒዝም እንቅስቃሴ በኋላ እየፈጠሩት ባለው ትብብር በአለም አቀፍ ደረጃ ያላቸው ተሰሚነት እየጨመረ መምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የኩባው ምክትል ፕሬዝዳንት ሳልቫዶር ቫልዴዝ በበኩላቸው ኩባ ከአፍሪካውያን ጋር ያላትን የቆየ ታሪካዊ ትስስር ማጠናከር እንደምትፈልግ ተናግረዋል፡፡

የጊኒው ፕሬዝዳንት አልፋ ኮንዴ ቀጣዩ የህብረቱን የሊቀመንበርነት ቦታ ከቻዱ ፕሬዝዳንት ኢድሪስ ዴቢ ተረክበዋል።

በጉባዔው መክፈቻ የኩባው ምክትል ፕሬዝዳንት ሳልቫዶር ቫልዴዝ፣ የፍልስጤሙ መሪ ሙሐሙድ አባስ እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ንግግር አድርገዋል።

ለሁለት ቀናት በሚካሄደው የመሪዎቹ ጉባዔ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበርና የሕብረቱ ምክትል ኮሚሽነርን ጨምሮ የሥራ አስፈፃሚ ምክር ቤቱ ምርጫም እንደሚካሄድ ይጠበቃል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy