Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በአዲስ አበባ ትናንት ምሽት የጎርፍ አደጋ ተከሰተ

0 476

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

በአዲስ አበባ ከተማ ትናንት ምሽት ሶስት ሰዓት ጀምሮ የጣለውን ዝናብ ተከትሎ በተለያዩ መኖሪያ ቤቶች የጎርፍ አደጋ ተከስቷል።

የጎርፍ አደጋው በዋናነት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስምንት መልካሼዲ ጀርባ፣ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሶስት ገርጂ ቴሌ ጀርባ እና ወረዳ ዘጠኝ ጎላጎል ጀርባ ተከስቷል።

ከዚህ ባለፈም በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ዳማ ሆቴል አካባቢ እና በክፍለ ከተማው ወረዳ 11 ፓስታና መኮረኒ አካባቢ በደረሰ የጎርፍ አደጋ በበርካታ መኖሪያ ቤቶች እና ንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል።

በአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መቆጣጠርና መከላከል ባለስልጣን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ፥ የባለስልጣኑ የአደጋ መከላከል ባለሙያዎች ሌሊቱን አደጋውን ለመከላከል ጥረት ማድረጋቸውን ተናግረዋል።

በዚህም ውሃውን ከቤት ውስጥ በማውጣትና የጎርፉን አቅጣጫ በማስቀየር በሰው ላይ አደጋ እንዳይደርስ ማድረጋቸውን ነው የተናገሩት።

በተጨማሪም ትናንት የዘነበውን ዝናብ ተከትሎ በተከሰተ አውሎ ንፋስ በርካታ የኤሌክትሪክ ትራንስፈርመሮች ላይ ጉዳት ደርሷል ብለዋል።

በተያያዘም ትናንት ምሽት 1 ሰአት ከ15 ደቂቃ ላይ ባልታወቀ ምክንያት በአባይ ትራንስፈርመር ማምረቻ ፋብሪካ ላይ በተከሰተ የእሳት አደጋ አንድ ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት ወድሟል።

በአደጋው ምክንያት ሊወድም የነበረና 50 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት ማዳን ተችሏልም ነው ያሉት አቶ ንጋቱ።

አቶ ንጋቱ አያይዘውም ለጎርፍ አደጋ በሚያጋልጡ አካባቢዎች የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ከወዲሁ ጥንቃቄ እንዲያደርጉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy