Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

አሜሪካ በኢራን ላይ ማዕቀብ ጣለች

0 778

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ኢራን ሰሞኑን የሚሳኤል ሙከራ ማድረጓን ተከትሎ በ13 ግለሰቦች እና ኩባንያዎች ላይ ማእቀብ መጣሏ ተሰማ፡፡

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቲውተር ገጻቸው ላይ ˝ኢራን በእሳት እተጫወተች ነው…ፕሬዚዳንት ኦባማ ለእነሱ ምንያህል ደግ እንደነበረ ዋጋ የሰጡት አይመስልም እኔ እንደዛ ግን አይደለሁም ፡፡˝ የሚል መልእክት አስፈረዋል፡፡

ኢራን በበኩሏ ለአሜሪካ ማስፈራሪያ እንደማትበገር አስታወቃለች፡፡

አሜሪካ የአሁኑ ማዕቀቧ ኢራን ለሽብርተኞች እና ተወንጫፊ ሚሳኤል ፕሮገራሟ በአካባቢው ሀገራት ፣በአጋሮቻችን እና በአለም አቀፍ ስጋት እየሆነች መጥታለች በሚል የተጣለ ነው ተብሏል፡፡

ማዕቀቡ የተጣለባቸው አዳዲሶቹ ቡድኖች በተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ፣ሊባኖስ ና ቻይና እንዲሁም በኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ አብዮታዊ ዘብ ኮር የሚገኙበት መሆኑን ዘገባው ያመለክታል፡፡

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማሀመድ ጃቫድ ዛሪፍ ሀገራቸው በአሜሪካ ማዕቀብን በዝምታ እንደማትቀበለው ተናግረዋል፡፡

˝ጦርነትን አንቀሰቅስም ሆኖም በራሳችን የመከላከል ብቃት እምነቱ አለን ˝ በማለት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ሳዑድ አረቢያ በበኩሏ ቴህራን በጎረቤት ሀገራት ማለትም በኢራቅ፣በሶሪያና የመን የምታደረገውን ጣልቃ ገብነት ማስቆም ያሰፈልጋል ማለቷ ተዘግቧል፡፡

ምንጭ፦ቢቢሲ

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy