Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

አዲስ ተሾሙ የስምንት ሀገራት አምባሳደሮች የሽኝት ፕሮግራም ተካሄደ።

0 641

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

አዲስ ተሾሙ የስምንት ሀገራት አምባሳደሮች የሽኝት ፕሮግራም ተካሄደ። በሽኝት ፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የኢፌድሪ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ለተሿሚዎቹ የስራ መመሪያ ሰጥተዋል። አዲስ ተሿሚ አምባሳደሮች የሃገሪቱን ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር በቁርጠኝነት ሊሰሩ እንደሚገባና አምባሳደሮች በሚሄዱባቸው ሃገራት ቀድሞ የነበረውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ በማጠናከር ለሃገራቸው ጥቅምና ዕድገት በትኩረት እንዲሰሩ እና አምባሳደሮቹ ከሃገራቱ ጋር ያለው የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካ ፣ የዲፕሎማሲ፣ የመግባባትና የወዳጅነት ግንኙነት እንዲቀጥል ከማድረግ ባሻገር ግንኙነቱን በማሳደግም የራሳቸውን አሻራ ማሳረፍ እንደሚገባቸው ተናግረዋል። አዲስ የተሾሙ አምባሰደሮች አቶ ሬድዋን ሁሴን በአየርላንድ ወይዘሮ ዘነቡ ታደሰ በጣልያን አቶ ቶሎሳ ሻጊ በኡጋንዳ፣ አቶ ፀጋዬ በርሄ በእስራኤል አቶ ረጋሳ ከፍአለ በጋና አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ በግብጽ አቶ አብዱልአዚዝ አህመድ በኩዌት አቶ ግርማ ተመስገን በኮትዲቯር የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው ያገለግላሉ። ፥”የሃገሪቱን የልማት ጉዞ የማስቀጠሉ ስራ በውስጥ በሚከናወኑ ተግባራት ላይ የተመሰረተ ቢሆንም የውጭ መልካም ዕድሎችና ተግዳሮቶች ያላቸው ተጽዕኖም ቀላል አይደለም” ያሉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ሲሆኑ ተጣለባቸውን የሕዝብና የመንግስት አደራ በብቃት ለመወጣት ተጨማሪ አቅምና መነሳሳት የሚፈጥርላቸው እንደሆነ የተናገሩት ደግሞ ተሿሚረ አምባሳደሮች ናቸው።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy