Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ኢትዮጵያ እያስመዘገበች ያለችው ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት የውጭ ባለሀብቶችን ትኩረት እየሳበ እንደሚገኝ ገልፍ ቱዴይ ዘገበ፡፡

0 417

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ኢትዮጵያ እያስመዘገበች ያለችው ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት የውጭ ባለሀብቶችን ትኩረት እየሳበ እንደሚገኝ ገልፍ ቱዴይ ዘገበ፡፡

ኢኮኖሚዋ በትክክለኛ ቅርፅ ላይ የሚገኘው ኢትዮጵያ በአለም ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ከሚያስመዘግቡ ሀገራት አንዷ እንድትሆን ፤ እንዲሁም ባለፉት አስር አመታት ባለሁለት አሃዝ እድገት እንድታስመዘግብ አስችሏታል ብሏል ዘገባው፡፡

በዱባይ የኢትዮጵያ ቆንሲል ጄኔራል የሆኑት ይበልጣል አዕምሮ ኢትዮጵያ የውጭ ባለሀብቶችን በመሳብ የተሻለች መዳረሻ እንድትሆን ያደረጓትን መሰረታዊ ነጥቦች ለገልፍ ቱዴይ ዘርዝረዋል፡፡

እነዚህም የፖሊቲካ እና ማህበራዊ መረጋጋት፤ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ፤ተስማሚ አየር እና ለም አፈር፤የግሉ ዘርፍ እና መንግስት ያላቸው ወዳጅነት፤ ርካሽ የሰው ኃይል, ተወዳዳሪ የማበረታቻ ጥቅል ሥራዎች እና ሰፊ የገበያ መዳረሻዎች መኖራቸው ነው ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ ኢንቨስት ለማድረግ ቅድሚያ የሚሰጣቸው የኢንዲስትሪ ዘርፎችንም አስቀምጠዋል፡፡

አግሮ-ፕሮሰሲንግ ኢንዱስትሪ, ጨርቃ ጨርቅና ልብስ ኢንዱስትሪዎች, ስኳር እና ተዛማጅ ኢንዱስትሪዎች, የኬሚካል ኢንዱስትሪ, በፋርማሲዩቲካል ኢንዱስትሪ ፤የብረታ ብረት እና ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪዎች ናቸው፡፡
ካውንስል ጀነራል ይበልጣል አያይዘውም ይህን ሊያስተናግዱ የሚችሉ የኢንዱስትሪ ፓርኮች መገንባታቸውን ገልፀዋል፡፡

በኢትዮጵያ እና በተባበሩት አረብ ኢሜሬትስ መካከል ያለው የንግድ እና ኢንቨስትመንት የሁለትዮሽ ግንኙነታቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱንም አረጋግጠዋል፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy