Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ወደ ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ በሚደረገው ሽግግር የሕብረት ስራ ማሕበራት የድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ተገለጸ

0 422

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ኢትዮጵያ ወደ ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ በምታደርገው መዋቅራዊ ሽግግር ውስጥ የሕብረት ስራ ማሕበራት የድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ገለጹ።

አራተኛው አገር አቀፍ የሕብረት ስራ ማሕበራት ኤግዚቢሽንና ባዛር በአዲስ አበባ ኤግዚቪሽን ማዕከል ተከፍቷል።

ከመላ አገሪቱ የተውጣጡ ከሶስት መቶ በላይ የሕብረት ስራ ማሕበራትና የግብአት አቅራቢ ተቋማት የሚሳተፉበት አራተኛው አገር አቀፍ የሕብረት ስራ ማሕበራት ኤግዚቪሽንና ባዛር ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በተገኙበት ተከፍቷል።

በባዛሩ በግብርና ምርቶች፣ የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ፣ በእደጥበብ እና ሌሎችም የስራ ዘርፎች ላይ የተሰማሩ የሕብረት ስራ ማሕበራት ምርትና አገልግሎታቸውን አቅርበዋል።

ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ኤግዚቪሽንና ባዛሩ የሕብረት ስራ ማሕበራት የደረሱበትን የእድገት ደረጃ የሚያሳይ መሆኑን ገልጸው ማሕበራቱ በአገሪቱ የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግር ውስጥ የድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ተናግረዋል።

መንግስት የሕብረት ስራ ማሕበራቱን ለማደራጀትና ለማጠናከር የሚረዱ የፖሊሲ እርምጃዎችን ከመውሰድ ጀምሮ የተለያዩ ድጋፎችን እያደረገ መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚንስትሩ ሕብረት ስራ ማሕበራቱም ሁለንተናዊ ተሳትፎ ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል።

የፌዴራል ሕብረት ስራ ማሕበራት ኤጄንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኡስማን ስሩር ኤግዚቪሽንና ባዛሩ በሕብረት ስራ ማሕበራትና ሸማቾች መካከል ዘላቂ የገበያ ትስስር ለመፍጠር መዘጋጀቱን ገልጸዋል።

የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚንስትሩ ዶክተር እያሱ አብርሀ በበኩላቸው ሕብረት ስራ ማሕበራት የከተማና የገጠሩን ሕብረተሰብ በተደራጀ መልኩ የሚያንቀሳቀሱ መሆናቸውን ገልጸው ያሉባቸውን ማነቆዎች ተፈተውላቸው ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆኑ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የድርሻቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል።

ተሳታፊ የሕብረት ስራ ማሕበራቱም ኤግዚቪሽንና ባዛሩ ተጠቃሚ እንደሚያደርጋቸው ተናግረዋል።

በአዲስ አበባ ኤግዚቪሽን ማዕከል የተከፈተው የሕብረት ስራ ማሕበራት ኤግዚቪሽንና ባዛር እስከ የካቲት 8/2009 ዓ.ም ይቆያል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy