Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የአሁኑ ትውልድ ድህነትን ለማሸነፍ በጀመረው ትግል አንጸባራቂውን የዓድዋ ድል እየደገመ ነው – መንግስት

0 732

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የአሁኑ ትውልድ ድህነትን ለማሸነፍ በጀመረው ትግል አንጸባራቂውን የዓድዋ ድል እየደገመ ነው አለ የመንግስት የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት።

ጽህፈት ቤቱ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው ሳምንታዊ የአቋም መግለጫው የፊታችን የካቲት 23 የሚከበረው የዓድዋ ድል ኢትዮጵያውያን ጀግኖች በዘመናዊ ጦር የታጠቀውን ወራሪ የጣልያን ጦር አሸንፈው ከሀገራችን ነጻነት አልፈው መላው የጥቁር ህዝብን ለነጻነት ማነሳሳታቸወን አስታውሷል።

የዛሬው ትውልድም በማሽቆልቆል ጉዞ ላይ የነበረችውን ሀገሩን ለመታደግ በህዳሴ ጉዞው ውስጥ ታላቅ ድልን በማስመዝገብ ላይ ይገኛል ይላል መግለጫው።

ድህነትን በመጋፈጥ በአዲሲቷ ኢትዮጵያ እየተረጋገጠ የሚገኘው ይህ ድል የአሁኑ ትውልድ ለአገሩ ክብር ያለው ቀናዒነት ውጤት መሆኑንም ጠቁሟል።

የዓድዋ ድል ለጥቁር ህዝቦች ነፃነት ምክንያት እንደነበረ ሁሉ ኢትዮጵያ አሁን እየተከተለችው ያለው ልማታዊ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት አፍሪካ በራሷ ፖሊሲ ማደግ እንደምትችል እያሳየ ነውም ብሏል ጽህፈት ቤቱ በመግለጫው ።

የዓድዋ ድል ሲከበርም የአሁኑ ትውልድ በተጀመረው የህዳሴ ጉዞ ድህነትን በማሸነፍ የአባቶቹን ታሪክ ለመድገም ቃሉን የሚያድስበት እንዲሆን ጽህፈት ቤቱ ጥሪውን አስተላልፏል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy