Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የኤርታሌ እሳተ ገሞራ

0 6,825

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

 በአፋር ክልል ደቡብ ምስራቅ ኤርታሌ በመጠኑም ይሁን በስፋቱ ከዚህ ቀደም ከነበረው የሚበልጥ አዲስ እሳተ ገሞራ መፈጠሩ ተነግሯል።

ርዝመቱ 5 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው አዲሱ የኤርታሌ እሳተ ገሞራ ሀይቅ ከዚህ ቀደም ከነበረው የኤርታሌ እሳተ ገሞራ ስፍራ 3 ኪሎ ሜትር ዝቅ ብሎ ይገኛል።

አዲሱ የኤርታሌ እሳተ ገሞራ በብዛት ዓለም አቀፍ ጎብኚዎችን እየሳበ ነው።

ertale_1.jpg

እሳተ ገሞራውን ከ1 ኪሎ ሜትር ርቀት ገደማ ላይ በመሆን መመልከት እንደሚቻልም ነው የተነገረው።

የኤርታሌ አዲሱ እሳተ ገሞራ በሰውም ሆነ በአካባቢ ላይ የከፋ ጉዳት የማስከተል አቅም እንደሌለው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስታውቋል።

የኤርታሌ እሳተ ገሞራ ትዕይንት በዓለም አስደናቂ በመሆኑ በርካታ ዘጋቢ ፊልሞች ተሰርተውበታል።

ertale_2.png

“በሌላው የዓለም ክፍል የሚፈጠር እሳተ ገሞራ ከፈነዳ በኋላ ጥቂት ጊዜ ቆይቶ የሚከስም ነው የኤርታሌ ትዕይንት ግን ከዓለም የተለየ የሚያደርገው ለረጅም ጊዜ መቆየቱ ነው”።

በኤርታሌ ቅርብ ርቀት ላይ የታየው አዲስ እሳተ ገሞራ እስካሁን በሰውም ሆነ በንብረት ላይ ምንም ዓይነት አደጋ አለመፍጠሩ ተገልጿል።

ዳሎል

በአፋር ክልል የሚገኘው ዳሎል ከዓለማችን ከባህር ወለል በታች 430 ጫማ (130 ሜትር) ዝቅታ ላይ ያለ ስፍራ ነው።

Dalol_ty.png

ከአዲስ አበባ 950 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው ዳሎል የዓለማችን ዝቅተኛ ቦታ መሆኑም ይነገርለታል።

ዳሎል ከዝቅተኛ ስፍራነቱ ባለፈ ግን ከፍተኛ የጨው ክምችት ያለበት እና የአሞሌ ጨው ንግድ በግመል የሚካሄድበት ስፍራ ነው።

DALOL_191.png

ከፍተኛ የፖታሽ ክምችት እንደሚገኝበትም ይነገራል።

Dalol_115.png

የፖታሽ ክምችቱም በየጊዜው በሚቀያይራቸው ቀለማት አሸብርቆ የሚታይ የዓለማችን ልዩ ስፍራ ነው።

Dalol_139.png

በፀጋ ታሪኩ

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy