Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ፕ/ት ሙላቱ ተሾመ አዲስ ለተሾሙ ስምንት አምባሳደሮች የስራ መመሪያ ሰጡ

0 356

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ኢትዮጵያን በተለያዩ አገራት ለሚወክሉ አዲስ ለተሾሙ ስምንት አምባሳደሮች የስራ መመሪያ ሰጡ።

ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ በሰጡት የስራ መመሪያ አምባሳደሮቹ በቆይታቸው የአገሪቱን ብሔራዊ ጥቅም በማስጠበቅና በሁለቱ መንግስታት መካከል ያለውን የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካና የዲፕሎማሲ ግንኙነቱን ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥረት ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ለአፍሪካ የምትሰጠውን ትኩረት ግምት ውስጥ በማስገባት በተለያዩ እህት የአፍሪካ አገሮች የተመደቡ አምባሳደሮች ተጨማሪ አደራ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

የስራ መመሪያ የተሰጣቸው አምባሰደሮች ሬድዋን ሁሴን በአየርላንድ፣ አምባሳደር ዘነቡ ታደሰ በጣሊያን፣ አምባሳደር ቶሎሳ ሻጊ በዩጋንዳ ሪፐብሊክ፣ አምባሳደር ጸጋይ በርሄ በእስራኤል፣ አምባሰደር ረጋሳ ከፍአለ በጋና፣ አምባሳደር ታየ አጽቀስላሴ በግብጽ አረብ ሪፐብሊክ፣ አምባሳደር አብዱል አዚዝ አህመድ በኩዌት እና አምባሳደር ግርማ ተመስገን በኮትዲቮር የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው የተሾሙት ናቸው። አምባሳደሮች ቃለ መሀላ ፈጽመዋል።

ሪፖርተር:-አማረ ተመስገን

 

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy