Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ህገ ወጥ የንግድ እንቅስቃሴን ለመከላከል በዘርፉ ያሉ አካላት ቅንጂታዊ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተገለጸ

0 437

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ህገ ወጥ የንግድ እንቅስቃሴን ለመከላከል በዘርፉ ያሉ አካላት ቅንጂታዊ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተገለጸ

 

ህገ ወጥ የንግድ እንቅስቃሴን ለመከላከል በዘርፉ ያሉ አካላት ቅንጂታዊ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የኢትዬጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ገለጸ፡፡

1ዐኛው ሀገር ዓቀፍ የግብር እና ቀረጥ ሣምንት በጂግጅጋ ከተማ በፓናል ውይይት መከበር ጀምሯል፡፡

የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ኃላፊ  ሚንስትር  አቶ ከበደ ጫኔ  በውይይቱ ላይ እንደገለፁት ህገ ወጥ የንግድ እንቅስቃሴ የአገር ኢኮኖሚን ይጎዳል፡፡

ባለፉት ዓመታት በተለይ የኢትዮጵያ ሱማሌ ክልል ህብረተሰብ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት ህገወጥ የንግድ እንቅስቃሴን ለመከላከል ባካሄደው ጥረት በመጠኑም ቢሆን ህጋዊ የግብይት ስርዓት እንዲይዝ ማገዙን ገልፀዋል፡፡

አሁንም ግን የኮንትሮባንድ ንግድ እንቅስቃሴ እንዳልቆመ የጠቆሙት  ሚንስትሩ “በህገ ወጥ መንገድ ወደ መሃል አገር የሚገቡ ሸቀጦች የአዲስ አበባ ገበያን እያጥለቀለቁት ነው “ብለዋል፡፡

ይህ ደግሞ በህጋዊ መንገድ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኘውን የንግድ ህብረተሰብ እየጐዳው መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

እንዲሁም ከቀረጥ ነፃ የሚገቡ መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎች በአግባቡ ለህብረተሰቡ እየደረሰ እንዳልሆነ ተናግረዋል፡፡

በተለይ ለኦሮሚያ ክልል ከፊል ዞኖች የተፈቀዱ መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎች በኢትዮዽያ ሶማሌ ክልል ከተሞች ሲሸጥ መገኘቱ ሚኒስትሩ መጥቀሳቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy