Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

አየር መንገዱ በተደራሽነት ከዓለም 11ኛ ደረጃን ያዘ

1 742

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዓለም አቀፍ ተደራሽነቱ 11ኛ ደረጃን ያዘ።

አየር መንገዱ ከመካከለኛው ምስራቅና ከአፍሪካ ሃገራት ደግሞ የመጀመሪያው ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ደረጃውን ሊያገኝ የቻለው ባለፈው ጥር ወር ባካሄደው ዓለም አቀፍ በረራ ነው ተብሏል።

ፍላይት ስቴትስ የተሰኘ ተቋም ባወጣው መረጃ መሰረት የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዓለም ላይ ካሉ አየር መንገዶች በወቅቱ ደንበኞቹ ጋር በመድረስ ከመካከለኛው ምስራቅና ከአፍሪካ የመጀመሪያው ሲሆን ከዓለም 11ኛ ደረጃን ይዟል።

አየር መንገዱ በጥር ወር 8 ሺህ ዓለም አቀፍ በረራዎች ያደረገ ሲሆን 81 በመቶ የሚሆኑት በአየር መንገዱ የጊዜ ዕቅድ መሰረት የተከናወኑ ናቸው።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም፥ አየር መንገዱ ከዓለም አስራ አንደኛ ከአፍሪካና ከመካከለኛው ምስራቅ ደግሞ 1ኛ ደረጃን ለመያዝ ያስቻለው የሰራተኞቹ ቁርጠኝነትና ታታሪነት መሆኑን ተናግረዋል።

አየር መንገዱ በ2016 በአፍሪካ ምርጥ አየር መንገድ ተብሎ “ስካይ ትራክስ” በተባለ ድርጅት መሸለሙ ይታወሳል።

በዓለም ላይ ከ90 በላይ መዳረሻዎች ያሉት የኢትዮጵያ አየር መንገድ፥ ካሉት ዘመናዊ አውሮፕላኖች በተጨማሪ በቅርቡ ሶስተኛውን ኤር ባስ ኤ 350 አውሮፕላን መረከቡን ኢዜአ በዘገባው አስታውሷል።

  1. Mulugeta Andargie says

    Well done!!! Well done!!! You are the leading company of all!!! Ethiopian Airlines!!! We proud of you!!! You are the major intrducers about your country!!! We don’t stop talking about you!!! Everywhere!!! Anywhere!!!! With a full confidence!!! Follow the American Airlines!!!

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy