ኢትዮጵያ በአለም አቀፉ የአካባቢ ጥበቃ አመቻች ድርጅት (ግሎባል ኢንቫይሮመንት ፋሲሊቲ) የውሳኔ ሰጪ አካል ውስጥ ተሳታፊ እንድትሆን ግብዣ ቀረበላት።
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ የድርጅቱን ዋና ስራ አስፈጻሚ በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
ኢትዮጵያ በአለም አቀፍ ደረጃ እያሳየችው ከምትገኘው ተጽዕኖ ፈጣሪነት አኳያ በድርጅቱ የውሳኔ ሰጪ አካል ውስጥ ተሳትፎ ቢኖራት የተሻለ መሆኑ ተገልጿል።
በዚሁ መሠረት ድርጅቱ ለኢትዮጵያ ግብዣ አድርጎላታል ነው የተባለው።
ውይይቱን የተከታተሉት የአካባቢ፣ የደንና የአየር ንብር ለውጥ ሚኒስትር ዶክተር ገመዶ ዳሌ እንደገለጹት፥ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለግብዣው አዎንታዊ ምላሽ ሰጥተዋል።
ድርጅቱ በቀጣይ ዓመት ጥቅምት ላይ የሚያዘጋጀው ጉባኤም በኢትዮጵያ እንዲደረግ ጠቅላይ ሚኒስትሩ መስማማታቸውን ተናግረዋል።