Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ኢትዮጵያ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሥር ያለች አትመስልም – የስብሰባው ታዳሚዎች Featured

0 408

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

“በኢትዮጵያ ያለው ሰላም፤ አገሪቱ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሥር ያለች አላስመሰላትም” ሲሉ የ28ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ስብሰባ ታዳሚዎች ተናገሩ።

የመሪዎቹ ስብሰባም በተለያዩ ኩነቶች ለየት ባለ መልኩ እንደተካሄደ የስብሰባው ተሳታፊዎች ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ባጋጠማት ሁከትና ግርግር ከመስከረም 28 ጀምሮ የአገሪቱን ሰላምና ደኅንነት ለመጠበቅ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጇ የሚታወስ ነው።

በመንግሥታቱ ድርጅት የአፍሪካ ልዩ አማካሪ ማገድ አብድላዚዝ ለኢዜአ እንዳሉት “አገሪቱ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሥር ያለች አትመስልም፤ ምንም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ምልክት የለም”።

በከተማዋ በተለያዩ ቦታዎች በመሄድ ምንም አይነት የጸጥታ ችግር እንዳላጋጠማቸውና ሌሎችም ወደፈለጉበት ቦታ ያለምንም ገደብና ቁጥጥር በመሄድ አገልግሎት ሲያገኙ መቆየታቸውን ገልጸዋል።

“ከዚህ በመለስ ስብሰባውም በሰላም ተጠናቋል፤ ሰላምን የሚያደፈርስ ምንም አይነት ችግር አላየሁም” በማለት አስተያየት ሰጥተዋል።

“ኢትዮጵያ ሕብረ-ብሄራዊት አገር ብትሆንም ሁሉም በአንድ ላይ የሚኖሩ ህዝቦች ናቸው” ያሉት አማካሪው “የተለያዩ አመለካከቶች በተለያዩ የአፍሪካ አገራት ይደመጣሉ፤ ይሁንና ይህም ኢትዮጵያን አልጎዳትም “ብለዋል።

28ኛው የመሪዎች ስብሰባ የተለየ እንደሆነና ስብሰባው የመንግሥታቱ ድርጅት ዋና ጸኃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝን መቀበሉን ለአብነት አንስተዋል።

የመንግሥታቱ ድርጅትና የአፍሪካ ኅብረት በሰላምና ደኅንነት፣ በልማት እንዲሁም በሰብዓዊ መብት ላይ ተቀራርበው እንዲሰሩ የሚያስችሉ ውሳኔዎች ተላልፈውበታል ነው ያሉት።

በኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝቦች ለስብሰባው ታዳሚዎች የተደረገውን እንግዳ አቀባበልም ምስጋና ሊቸራቸው ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።

በአፍሪካ ኅብረት የኢንዱስትሪ ክፍል ኃላፊ ሃሰን ሁሴን በበኩላቸው “በኢትዮጵያ ሰላም አለ፤ በአገሪቱ ያለው ሁኔታም መልካም ነው” ብለዋል።

ይህም አገሪቱ ሰላምና ልማት በማረጋገጥ ረገድ በትክክለኛ ጎዳና ላይ መሆኗን አመላካች እንደሆነ ጠቁመዋል።

ስብሰባው በሰላም እንዲጠናቀቅ የኢትዮጵያ መንግሥት የጸጥታ ኃይሎችን በተገቢው መልኩ በመመደብ የተደረገው ርብርብ የሚበረታታ መሆኑን አንስተዋል።

በዚህም ስብሰባው በሰላም ለማጠናቀቅ መቻሉን ነው ያስረዱት።

28ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ስብሰባ፤ የኅብረቱን ሊቀ መንበርና ሌሎች በርካታ አህጉራዊ ውሳኔዎችን በማሳለፍ በትላንትናው ዕለት ተጠናቋል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy