Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የሚንስትሮች ምክር ቤት በመንግስት ሰራተኞች የደመወዝ ማስተካከያ ጥናት ላይ ውሳኔ አሳለፈ

0 2,728

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የሚንስትሮች ምክር ቤት የመንግስት ሰራተኞች ደመወዝና የጡረተኞች አበል ማስተካከያ ከጥር አንድ ጀምሮ እንዲተገበር ወሰነ፡፡

የሚንስትሮች ምክር ቤት ባካሄደው 22ኛ መደበኛ ስብሰባ በመንግስት ሠራተኞች የደመወዝ ማስተካከያ ጥናት፣ በመንግስትና በግል ሰራተኞች ጡረተኞች የአበል ጭማሪ፣ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽንን ለማቋቋም በተዘጋጀ ረቂቅ ደንብ እና ኢትዮጵያ ከተለያዩ አለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር በተስማማችባቸው የብድር ስምምነቶች ላይ ተወያይቶ ውሣኔ አሳልፏል፡፡

ለመንግስት ሰራተኞች የደመዎዝ ማስተካከያ እንዲደረግ መንግስት በገባው ቃል መሠረት በፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ሚኒስቴር ተዘጋጅቶ በቀረበው የደመዎዝ ማስተካከያ ጥናት ላይ ምክር ቤቱ በስፋት ከተወያየ በኋላ ማስተካከያው ከጥር 1 ቀን 2ዐዐ9 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ ወስኗል፡፡

ምክር ቤቱ ከዚህም በተጨማሪ በጡረተኞች የአበል ጭማሪ ላይ ተወያይቶ ጭማሪው ከጥር 1 ቀን 2ዐዐ9 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንደደረግ ወስኗል፡፡

የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽንን በተመለከተ ከሀገሪቱ ፈጣን እድገት አንፃር በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ ከመጣው የከተሞች እድገት ጋር የሚታየውን የመኖሪያ ቤት እጥረት ለመቅረፍ መንግስት የከተማ ልማት ፖሊሲን መሠረት በማድረግ የከተማ ቤት አቅርቦት የስትራቴጂ ማእቀፍ ቀርጾ ተግባራዊ በማድረግ የቤት ፍላጎትን ከአቅርቦት ጋር የተጣጣመ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱን ገልጿል፡፡

ከዚህ ቀደም የነበረው የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ አደረጃጀትን የአሰራርና የሰው ሃይል ችግሮችን በመፍታት ተቋሙ ተልእኮውን በውጤታማነት ለመፈፀም እንዲችል ጥናት የተደረገ ሲሆን በጥናቱ ውጤት መሰረትም የኤጀንሲው አደረጃጀት መቀየር ያለበት መሆኑ ስለተረጋገጠ በገበያ ሂሣብ ቤቶችን ማልማት፣ ማከራየት፣ መጠገንና ማስተዳደር ተልእኮ ያለው የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ማቋቋሚያ ረቂቅ ደንብ ተዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቧል፡፡

ምክር ቤቱ በቀረበው ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ ማሻሻያዎችን በማከል ደንቡ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ እንዲወጣና በሥራ ላይ እንደውል ወስኗል፡፡

ኢትዮጵያ ከተለያዩ አለም አቀፍ ድርጅቶችና ተቋማት ጋር በመስኖ ልማት፣ በመጠጥ ውሃ ፣ በመንገድ ግንባታ፣ በኤሌክትሪክ አገልግሎት እና በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ተርሚናል ፕሮጀክቶች  ማስፈፀሚያ ያደረገቻቸውን የብድር ስምምነቶችም  ከአገሪቱ የብድር ስትራቴጂ ጋር የሚጣጣሙ በመሆናቸው ይፀድቁ  ዘንድ  ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ መወሰኑን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy